“በሰሓርቲ ወረዳ ነዋሪዎች በሰራዊቱ የተፈጸመ በደል የለም፣ የጸጥታ ሀይሉን እና አመራሩን ሆን ተብሎ ከህዝብ ለመነጠል እየተሰራ ነው” ሲል የክልሉ የጸጥታ ቢሮ አስተባበለ
#FastMereja I በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሀይሎችን እና አመራሮቻቸውን ስም በማጥፋት ሆን ተብሎ ከህዝብ ለመነጠል እየተሰራ ነው ሲል የትግራይ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሰሃርቲ ወረዳ የተፈጸመውን ሁከት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስተባበለ፤ “በጸጥታ ሀይሉ ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እና ስሙን በማጥፋት ከህዝብ ለመነጠል የሚደረግ ከንቱ ድካም” ሲል ገልጿል።
ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ “የተወሰኑ የትግራይ ሠራዊት አመራሮች” ሲል የጠራቸው አካላት “የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅር ለማፍረስ አግባብነት የሌለው ስራ እየሰሩ ይገኛል” ሲል መውቀሱን መዘገባችን ይታወሳል።
የክልሉ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ የካቲት 15 ቀን ባወጣው መግለጫ በሰሃርቲ ወረዳ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት እና ግርግር “ወደ ሌላ መልክ እና ደም አፋሳሽ ተግባር እንዳይቀየር” በማድረግ የጸጥታ ሀይሉ ሁኔታውን ለማርገብ ቻለ እንጂ በህዝቡ ላይ የፈጸመው አንዳችም በደል የለም ሲል አስተባብሏል፤ እንዲያውም በጸጥታ ሀይሎቹ ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ስም ማጥፋት ተፈጽሞብኛል ሲል ኮንኗል።
Via Addis Standard #ፖለቲካ
