banner

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የF35 RC ጀት በረራ ተሳካ

​#FastMereja I ወጣቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ኢብራሂም አሊ (Ibrahim Ali)፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን የF35 RC የጀት ሞዴል በተሳካ ሁኔታ ማብረር መቻሉን አስታወቀ።

​ወጣቱ የፈጠራ ሰው ይህ ውጤት የተመዘገበው ተከታታይ ጥረትና ትግል ከተደረገ በኋላ መሆኑን ገልጾ፤ “ይህ የጀት ፕሮጀክት ከ8 ሙከራዎች በኋላ በ9ኛው በተሳካ ሁኔታ ከመሬት ተነስቶ በረረ” ሲል የጉዞውን ፈታኝነት አስረድቷል።

​ከትንሽ ጅማሮ ወደ ትልቅ የአየር ቴክኖሎጂ ኃይል
​ኢብራሂም አሊ ለስራው መነሻ ያደረገው የቱርክን የድሮን ቴክኖሎጂ አብዮት የመራውን የሰልቹክ ባይራክታር (Selçuk Bayraktar) ታሪክ መሆኑን ገልጿል። ባይራክታር እ.ኤ.አ. በ2005 በትንሽ የድሮን ፕሮቶታይፕ ጀምሮ ዛሬ ቱርክን በዘርፉ የዓለም ኃያል እንዳደረጋት ሁሉ፣ የእሱም ራዕይ ኢትዮጵያን በአየር ቴክኖሎጂ ጠንካራ ኃይል ማድረግ እንደሆነ ገልጿል።

​”ዛሬ በትንንሽ የሪሞት ኮንትሮል ጀቶች እንጀምራለን፤ ነገ ግን የኢትዮጵያን አየር ኃይልና አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ለማጠናከር የሚረዳ ትልቅ ተቋም እንገነባለን” ሲል የወደፊት ተስፋውን አጋርቷል።

#ሳይ_ቴክ

Leave a Comment