banner

በቤት ኪራይ ምክንያት የተከራዩን ጥርስ የሰበረው አከራይ 6 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

#FastMereja I የዎላይታ ሶዶ ከተማ አረዳ ክፍለ ከተማ ህብረት ቀበሌ ውስጥ በቤት ኪራይ ምክንያት የተከራዩን ጥርስ የሰበረው አከራይ 6 ዓመት ከ 6ወር ጽኑ እስራት መቀጣቱን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ደርጉ አሳሌ ገልጸዋል ።

ተከሣሽ ኤልያስ ባሣ አኔቦ በቀን 03/06/2018 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ በህብረት ቀበሌ ውስጥ በቤት ኪራይ ምክንያት ነበር ከተከራይ ጋር በመጣላት በቦክስ የላይኛውን ሁለት የፊት ጥርሱን ሊሰብር የቻለው።

ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ወደ ዐ/ህግ በመላክ ፋይል መክፈቱን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ታክቲክ ምርመራ ሃላፊ ተወካይ ኢ/ር ጌታቸው ወ/ዮሐንስ ተናግረዋል።

በመሆኑም የወላይታ ሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደ/ፍ/ቤት በሰዉና በሀኪም ማስረጃ ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በቀን 03/07/2018 ዓ/ም ባዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሣሹ ላይ የ 6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት መወሰኑን ኢ/ር ጌታቸው ገልጸዋል ሲል ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ነው የዘገበው።

#ችሎት

Leave a Comment