0
#FastMereja I የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በደረሰው የተገልጋይ ጥቆማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ አያለው እንዲሁም የነዋሪ መረጃ፣ ህትመት ስርጭት እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ እጅጉ በጋራ በመመሳጠር ላለተገባ ሰው አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ በ10ሺ ብር ተደራድረው የዲጂታል ምዝገባ በማከናወን ላይ ሳሉ በተደረገው ክትትል እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
የተቋሙ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር ላለፉት ሶስት የስራ ቀናት ክትትል ሲያደርግ በመቆየት ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ የካቲት 17 በጽ/ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ተቋሙ በክትትሉ የተደራጁ የድምፅ ቅጂ እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፖሊስ አስረክቧል።
#ችሎት

3 comments
አለመያዙ ነው እንጅ ሁሉም ሌባ ነው😀😀😀
ፎቶ እንፈልጋለን
ፎቶ የላቸውም ከእኔም እንዳይቀበሉ