#FastMereja I አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር ከኖታ መኪና አስመጪ ጋር በመተባበር ለአባላቱ የኤሌክትሪክ መኪና ብድር በማመቻቸት በዛሬው ዕለት የርክክብ ስነ ስርዓት አካሄዷል።
ማህበሩ ከተለያዩ የመኪና አስመጪዎች በመነጋገር የመኪና ብድር አገልግሎት በስፋት ለአባላቱ እየሰጠ የማገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከዚህ ቀደም በተለየያዩ ከተሞች ከኖታ መኪና አስመጪ እና ከሌሎች አስመጪዎች ጋር በመተባበር ለአባላቱ 200 የኤሌክትሪክ መኪኖች አስረክቧል ተብሏል።
ማህበሩ መንግስት ያስቀመጠውን ቴክኖሎጂ መር የሆነ አቅጣጫ በመከተል ከተለያዩ የመኪና አስመጪዎች ጋር በዋጋ፣ በቅልጥፍና እና በምቾት ቀዳሚ የሆነውን የኤሌክትሪክ መኪና ለአባላቱ የፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን አባላቱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ተበድረው እንዲገዙ ማመቻቸት ብቻ ሳይሆን በቁጠባም የተሻለ አማራጮችን በማቅረብ ለራሳቸውም ለሌቹም ስራ ዕድል እየፈጠሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ማህበሩ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት አድማሱ በማስፋት ለአባላቱ የተለያዩ የብድር አማራጮች በማቅረብ ለማገልገል ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ትግበራ እንደገባ የተጠቆመ ሲሆን ለዚህም አባላቶቹ የሚገባቸውን የቁጠባ መጠን በማሟላት አገልግሎቱን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪውን አስተላልፏል።
#ቢዝነስ




