banner

በአረብ ሀገር በቤት ሠራተኝነት እስከ ሚሊዮን ስኬት

#FastMereja I በአረብ ሀገር በቤት ሠራተኝነት በነበረችበት ወቅት ከባድ ሰቆቃና ድብደባ ያሳለፈችው ወይንሸት አየነው፡ ሁሉንም ፈተናዎች በጽናት በመወጣት ሁለተኛውን የሕዝብና የባህል አልባሳት መሸጫ ሱቋን በዛሬው ዕለት በመሃል 22 መርካቶ ህንፃ በይፋ አስመርቃለች። ከስደት መልስ በ40 ሺህ ብር ብድር የጀመረችውን የንግድ እንቅስቃሴ በጊዜ ሂደት በማሳደግ፤ ዛሬ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ሀገር በቀልና ዘመናዊ አልባሳትን በማምረት ወደ አሜሪካ፣ ካናዳ እና እንግሊዝ መላክ መቻሏን በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

በዚሁ የመርካቶ ህንፃ የቅርንጫፍ ምረቃ መርሃ ግብር ላይ የወይንሸት ወላጆች፣ ድምፃዊ ሰለሞን ተካ እና የፋና ላምሮት ዳኛ ብሩክ በመገኘት ሪቫን የቆረጡ ሲሆን፤ የቅርብ ጓደኛዋ ድምፃዊት ትዕግስት አስማረ የወይንሸትን የጽናትና የታጋሽነት የሕይወት ጉዞ በእንባ ታጅባ ለታዳሚው አቅርባለች። ተቋሙ “ግዮን የባህል አልባሳት” በሚል መጠሪያው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ከወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖችም ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የባህል አልባሳት ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።

ወይንሸት በትውልድ ከተማዋ ቲሊሊ ለወላጆቿ ዘመናዊ ቤት ሰርታ ማረከቧ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም የንግድ ሥራዋን ወደ አሜሪካ አትላንታ ለማስፋፋት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ተናግራለች። በዛሬው ዕለት የተካሄደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የንግድ ስኬትን ከማብሰር ባለፈ የመከራ፣ የጽናትና የተስፋ ፍሬ የታየበት ታሪካዊ መድረክ ሆኖ ማጠናቀቁን የፋስት መረጃ የዝግጅት ክፍል ዘግቧል።

#ቢዝነስ





1 comment

Raggaasaa Abbaa Fira'aans November 10, 2026 - 7:05 pm

Great picture ❣️

Reply

Leave a Comment