0
#FastMereja I በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረ ስብከት በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባው ቆርቋት 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
ትምህርት ቤቱ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረ ስብከት ሙሉ ወጪ የተገነባ ሲሆን ከ17 ሚሊየን 976 ሺህ ብር በላይ የፈጀ ነው።
ግንባታውም አምስት የመማሪያ ክፍሎችን፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችን፣ ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤትና የውሃ መሰረተ ልማትን ያካተተ ሲሆን ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ከ650 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።




