banner

“በረካ ሆምስ ሪል እስቴት በ18 ወራት ውስጥ ወደ 1,000 የሚጠጉ ቤቶችን አጠናቅቆ ለባለቤቶቻቸው ለማስረከብ ዕቅድ ይዟል”

#FastMereja I በስምንት ዓመታት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ማከናወኑን የገለጸው በረካ ሆምስ ሪል እስቴት፣ የሥራ አፈጻጸሙንና የቀጣይ የማስፋፊያ ዕቅዶቹን ትላንት ሕዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል ባካሄደው ልዩ መርሐ ግብር ይፋ አደረገ።

በ2011 ዓ.ም. በአንድ መሐንዲስና ሰባት በማይሞሉ ሠራተኞች በጋርመንት አካባቢ ባለ 16 ቤቶች ሕንፃ ሥራውን የጀመረው ተቋሙ፣ ዛሬ ላይ 16 መሐንዲሶችንና ከ250 በላይ ሠራተኞችን ወደያዘ ግዙፍ ተቋም ማደጉን የድርጅቱ የማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ ተመስገን ታምራት በመድረኩ ላይ ገልጸዋል። ድርጅቱ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ከ305 በላይ ዜጎችን የቤት ባለቤት ማድረግ መቻሉም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት በ15 ሕንፃዎች ላይ የግንባታ ሥራ እያከናወነ የሚገኘው በረካ ሆምስ፣ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ወደ 1,000 የሚጠጉ ቤቶችን አጠናቅቆ ለባለቤቶቻቸው ለማስረከብ ዕቅድ ይዟል። ከዚህም ባለፈ በቄራ፣ ካዛንቺስ፣ ሳርቤትና ጀርመን አካባቢዎች አዳዲስ የመኖሪያና የንግድ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የያዘውን ዕቅድና የአዲሱን ሳይት ዲዛይን ለታዳሚዎች አስተዋውቋል።

ከመርሐ ግብሩ ጎን ለጎን ድርጅቱ ለደንበኞቹ ልዩ የዋጋ ማሻሻያ ማቅረቡን የበረካ ሆምስ የሽያጭ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሐይለማርያም ለጥአርጌ አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት ደንበኞች በእያንዳንዱ ካሬ ሜትር ላይ የ10 ሺህ ብር ቅናሽ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም የግንባታ አድማሱን በማስፋት ለበርካታ ዜጎች የቤት ባለቤትነትና የሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።





Leave a Comment