banner

ላይፍታይም ፕሮፐርቲ አዲሱን «ቦሌ አይኮኒክ» ሳይት በይፋ አስጀመረ፣ ለቦሌ ግራንዲየር ቅንጡ መኖሪያ ሕንፃ ካርታ አስረክበዋል!

ላይፍታይም ፕሮፐርቲ አዲሱን «ቦሌ አይኮኒክ» ሳይት በይፋ አስጀመረ፣ ለቦሌ ግራንዲየር ቅንጡ መኖሪያ ሕንፃ ካርታ አስረክበዋል!

#FastMereja – ላይፍታይም ፕሮፐርቲ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በማዕከላዊ ቦሌ የሚገነባውን ዘመናዊ «ቦሌ አይኮኒክ» 3B+G+16 የመኖሪያ እና የኢንቨስትመንት ሕንፃ ግንባታ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ድርጅቱ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ አዲሱን ፕሮጀክት ከማስጀመሩ ባለፈ፣ ግንባታው ወደ መጠናቀቅ ለተቃረበውና 2B+G+22 ከፍታ ላለው «ቦሌ ግራንዲየር» ቅንጡ መኖሪያ ሕንፃ ገዢዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመድረክ ላይ አስረክቧል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሰውአለ አባተ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ ትልቁ ሀብት እምነት፣ ጥራት እና ቃልን በወቅቱ መፈጸም መሆኑን ገልጸው፣ ለደንበኞች የተበረከተው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የዚህ ሕያው ምስክር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የድርጅቱ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደግሰው አያና በበኩላቸው፣ ዋናው ራዕያቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ስጋት ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል በ4 ኪሎ ወዳጅነት ፓርክ አካባቢ የገነባውን የመኖሪያ ሕንፃ በወቅቱ አጠናቆ ያስረከበው ላይፍታይም ፕሮፐርቲ ትሬዲንግ፣ ዛሬ የግንባታና የሽያጭ ምዕራፉን በይፋ ያበሰረለት «ቦሌ አይኮኒክ» ሳይት ከማዶ ሆቴል ጀርባ የሚገኝ ሲሆን፣ ለሀገር ውስጥና ለዲያስፖራ ገዢዎች ከፍተኛ የኢንቨስትመንት አማራጭ ይዞ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።





Leave a Comment