banner

ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

#FastMereja I ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ዛሬ ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም በራስ ሆቴል ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለጸው ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ በተለየ ሁኔታ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ እና በዘርፉ ላይ ያተኮረ የፋይናንስ አገልግሎት ዋነኛ አቅራቢ ለመሆን ዝግጅት መጠናቀቁ ተነግሯል

ወገን የተቋቋመበት ዋና አላማ በህጉ የተፈቀዱ ማንኛውንም አነስተኛ የፋይናንስ፣ የኢንሹራንስ እና ተዛማጅ አገልግሎቶችን በከተማና በገጠር ለሚገኙ በትራንስፖርት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም በሌሎች የንግድ ስራ መስኮች ለተሰማሩ ሰዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማህበሩ ባለ አክሲዮኖች፣ ለደንበኞችና ለሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የኢኮኖሚ ጥቅም ማስገኘት እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

ለወገን ማይከሮ ፋይናንስ የተመሰረተው 39.3 ሚሊዮን ብር የተፈረመ እና 10.3 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል በማስመዝገብ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የተከፈለ ካፒታል 21.6 ሚሊዮን ብር ደርሷል።

#ቢዝነስ





Leave a Comment