banner

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ

#FastMereja I የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ÷ አየር መንገዱ ዘመኑን የዋጀ አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው።

በዓመቱ 6 ዓለም አቀፍ ጣቢያዎች መክፈት የቻለው አየር መንገዱ፥ 13 የተለያዩ አውሮፕላኖች ወደ ስራ አስገብቷል ነው ያሉት።

በ2017 በጀት ዓመት 19 ሚሊየን መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጓጓዛቸውን ነው የተናገሩት።

ከመንገደኞችና ዕቃ ጭነት አገልግሎትም 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም አመልክተዋል።

በዓመቱ በዘርፉ በርካታ አሉታዊ ክስተቶች መከሰታቸውን አንስተው በተለይም በተለያዩ ሀገራት በተፈጠረው ጦርነት በረራዎች ተስተጓጉለዋል ብለዋል።

የኤፍ.ኤም.ሲ ዘገባ እንዳመላከተው አሁን ላይ የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎች 21 መሆናቸውን ጠቁመው፥ በቅርቡ የሚጠናቀቁ የ5 መዳረሻዎች ግንባታ እየተከናወነ ነው።

#ቢዝነስ

3 comments

ፍቅር ያሸንፋል August 5, 2025 - 8:16 am

አክፍሉን

Reply
Joe Be August 5, 2025 - 8:16 am

ከ Jon Daniel ነው አ😅

Reply
ሮዛ ፓርክስ August 5, 2025 - 8:16 am

እሱም እንደ ቴሌ የነፃ የአሜሪካ ጉዞ ትኬት ቢሸልመን 😎

Reply

Leave a Comment