banner

የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ ወደ 17 በመቶ እንዲያድግ ምክረ ሃሳብ ቀረበ

#FastMereja I በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሆነውን የግብር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ጥምርታን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት፣ የሀገሪቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምጣኔን ከ15% ወደ 17.5% እንዲያድግ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ታወቀ።

ይህንን የግብር ምጣኔ ማሳደግ፣ የሀገሪቱን የግብር ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሳድግ እንደሚችል ተነግሯል።

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፊስካል ጥናት ተቋም (IFS) በጋራ ባዘጋጁት አዲስ ጥናት፣ የኢትዮጵያ የ15% የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ ከብዙ የምስራቅ አፍሪካ እና የደቡብ ሰሃራ አፍሪካ ሀገራት ምጣኔዎች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ነው።

ለምሳሌ፣ የኬንያ የ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምጣኔ 16% ሲሆን፣ የሩዋንዳና የዩጋንዳ ደግሞ 18% ነው። የደቡብ ሰሃራ አፍሪካ ሀገራት አማካይ ምጣኔም 17.5% መሆኑን አመልክቷል።

ጥናቱ አክሎም፣ የ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔን ወደ 17.5% ማሳደግ ብቻ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በተጨማሪ 0.4% ነጥቦችን ከ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስገኝ እንደሚችል ጠቁሟል።

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከዚህ በፊት ታክስ አልተሰበሰበባቸው የነበሩ እንደ ነዳጅ ያሉ ምርቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ መጀመሩ ትልቅ አዎንታዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

“የኢትዮጵያ ታክስ-ለ-ጂ.ዲ.ፒ ምጣኔ፡ የማነፃፀሪያ ግምት እና የአፈጻጸም ትንተና” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ጥናት፣ የኢትዮጵያ የታክስ-ለ-ጂ.ዲ.ፒ ምጣኔ በ2022/23 በጀት ዓመት ወደ 7.5% ዝቅ ማለቱን ያሳያል።

ይህ ቁጥር በ2014/15 ከነበረው ከፍተኛው 12.4% ጋር ሲነፃፀር 4.9 በመቶ ነጥብ ቅናሽ አሳይቷል። ለዚህ ከፍተኛ የገቢ ቅናሽ ዋና ዋና ምክንያቶችም ዉስጥ ​መዋቅራዊ ለውጦች ፣​የፖሊሲ ልዩነቶች እና ​ዝቅተኛ የታክስ ተገዢነት መሆናቸውን በዝርዝር አስቀምጧል።

Via: Capital

#ቢዝነስ

10 comments

Ahmed Bihonegn August 15, 2025 - 5:55 pm

ምክር ቤት ከገባ ፅደቀ 😉😉😉

Reply
Dige A Wagiso August 15, 2025 - 5:55 pm

መንግስት ቸግሮታል😅

ጭራሽ 17%😅 መንግስታዊ ቅፈላ ይሉሀል😌

Reply
Melaku Gebeye August 15, 2025 - 5:56 pm

ምነዋ ለደመወዝ ሲሆን ከኬንያ ጋር አታወዳድሩን አላችሁን ታድያ🤔🤔🤔

Reply
Mila Mulugeta August 15, 2025 - 5:56 pm

የጉድ ሀገር😢😢😢😢

Reply
Helamo Heleebo August 15, 2025 - 5:57 pm

ምክራቸው ይፍረስ እነዚህማ መካሪ ሳይሆኑ ጋንግሪን ናቸው💀💀💀

Reply
Sebahudin Nesro August 15, 2025 - 5:58 pm

ነጋዴዉን ብኔድ ይሻለናል የሚያስብል ሀሳብ ነዉ😂

Reply
DM DW August 15, 2025 - 5:58 pm

አረ ህዝቡን ኣታሳቃዩት ተው

Reply
Habtamu Tesfaye August 15, 2025 - 5:58 pm

ለምን 71% አትደርጉም

Reply
Mülë Řøŵ August 15, 2025 - 5:58 pm

በጣም አሪፍ ሊበረታታ የሚገባ 😂😂 ይላል አሁን ያ የጓጥ ቀበሌ አስተዳደር ይመጣና 😂😂😂

Reply
ወዳ ጅሲ ከዳ August 15, 2025 - 5:58 pm

IMF ገመድ በመንግስት አንገት ላይ እያጠበቀ ነው በለኛ

Reply

Leave a Comment