0
#FastMereja I ከ10 አመት በፊት በባህል አልባሳት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ከ251በላይ ባለሙያዎች ከ200 ብር ጀምሮ በመቆጠብ አዲስ በተሰራው የሽሮሜዳ አደባባይ ፊትለፊት የሰሩት ግዙፍ የባህል አልባሳት መሸጫ የገበያ ማዕከል በመገንባት ዛሬ በድምቀት አስመርቀዋል።
ባለሙያዎቹ በመቆጠብ ለሽሮሜዳና አካባቢው ተጨማሪ ድምቀት የሆነውን ግዙፍ ህንፃ በመገንባት የሱቅ ባለቤት ከመሆናቸውም በላይ የብሄር ብሄረሰብ የባህል አልባሳትን ጨምሮ በዲዛይነር የሚሰሩ አልባሳትን በአይነትና በብዛት በአንድ ቦታ የያዘው ይህ የገበያ መዕከል ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ጎብኝዎች ከዛሬ ጀምሮ ክፍት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በእለቱም ለአንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ለጋዜጠኞች የባህል አልባሳትንም በስጦታ አበርክቷል።
#ቢዝነስ




