banner

ኢትዮ ቴሌኮም በ3 አመት ውስጥ የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 100 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዷል።

#FastMereja I ኢትዮ ቴሌኮም “ቀጣዩ አድማስ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ” የተሰኘ አዲስ የሶስት አመት ስትራቴጂ እና የ2018 በጀት ዓመት የቢዝነስ እቅድ ዛሬ ነሃሴ 20/2017 ዓ.ም ይፋ አደረገ።

የኩባንያውን እቅድ ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቀጣዩ አድማስ ስትራቴጂ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 2025 እስከ ሰኔ 2028 ያለውን የሶስት ዓመት ጊዜ የሚሸፍን እንደሆነ ገልጸው የሀገራችንን እና ከዚያም ባሻገር ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሚና ለማጠናከር ያለመ ሲሆን ትኩረቱን የደንበኞችን ተሞክሮ በማሻሻል፣ ኔትወርኮችን በማዘመን እና ዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት፣ በአስተማማኝ የመረጃ ደህንነት፣ የገቢ ምንጮችን በማስፋፋት፣ የሰው ኃይልን በማጎልበት እና የአሰራር ብቃትን በማሳደግ፣ የመሪነት ቦታውን በማስጠበቅ፣ ቴሌብርን በማሳደግ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚጠቀሙ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት እና ዘላቂነት ባላቸው አጋርነቶችና
በአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት ላይ ትኩረት በማድረግ ለደንበኞቹ፣ ለባለአክሲዮኖቹ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ዘላቂ እሴት መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ተናግሯል።

በ2018 በጀት ዓመት የደንበኞቹን ብዛት በ6% በመጨመር 88 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን በሞባይል ድምጽ 6% በመጨመር 85.4 ሚሊዮን፣ በሞባይል ዳታና ኢንተርኔት በ13.3% በመጨመር 52.8 ሚሊዮን እንዲሁም የመደበኛ ብሮድባንድ ደንበኛ በ23% በመጨመር 1 ሚሊዮን በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርዓት መጠንን 77.2% ለማድረስ ታቅዷል፡፡

የሞባይል ብሮድባንድ በተለይም የ4ጂ ሽፋን ከ71% ወደ 85% በማሳደግ እና የ5ጂ አገልግሎት በማስፋፋት ለ1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል አቅም ይገነባል ተብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 235.8 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ያቀደ ሲሆን ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ45.6% ጭማሪ አለው፡፡ ከዋናው የቴሌኮም አገልግሎቶች በ133 ቢሊዮን ብር ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙ ሲሆን፣ ወደ 40% የሚጠጋው ገቢ ደግሞ ከመደበኛ ቴሌኮም ባሻገር ካሉ የቢዝነስ ሥራዎች ለማግኘት ታቅዷል፡፡

የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር በ14% በማሳደግ 62.5 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን የግብይት መጠኑም ወደ 4.43 ትሪሊዮን ብር ወይም በ86% ለማሳደግ እና የግብይት ብዛቱ ወደ 1.94 ቢሊዮን ወይም በ83% ለማሳደግ ታቅዷል።

ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ማብቂያ አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 100 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዷል።

በስትራቴጂ ዘመኑ ማጠናቀቂያ የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር በ36.8% በማደግ 75 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን የግብይት መጠኑም ወደ 21.3 ትሪሊዮን ብር (+334%) እና የግብይት ብዛቱ ወደ 10.4 ቢሊዮን (+439%) ለማሳደግ ታቅዷል። ከቴሌብር የሚገኘው ገቢ ወደ 49.1 ቢሊዮን ብር (+568%) ለማሳደግ እንዲሁም የንግድ አጋሮች ቁጥርን ወደ 960.6 ሺህ (+209%) እና ወኪሎችን ወደ 840 ሺህ (+162%) በማሳደግ የቴሌብርን ስነ-ምህዳር ለማጠናከር ታቅዷል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያለውን አበርክቶ ከመወጣት አኳያ ከአገልግሎቱ ባሻገር በሦስቱ ዓመታት ውስጥ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆነ ታክስ በድምሩ 253 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የትርፍ ድርሻ ክፍያ (ዲቪደንድ) በመፈጸም በድምሩ 111.3 ቢሊዮን ብር ለመንግስት ፈሰስ ለማድረግ ታቅዷል።

#ቢዝነስ




4 comments

Er Mi August 26, 2025 - 10:22 am

LinkedIn አካውንት አለዎት!? አይጠቀሙበትም? እንግዲያውስ ያከራዩት:
👑100+ ኮኔክሽንና 1 ዓመት የሞላው ከሆነ ½ ክፍያ ሳምንት ሳይጠብቁ ወዲያው ይደርስዎታል።
-እድሜው 3 ወር በ300+ ኮኔክሽን ወይም
-6 ወር ያለፈውና ኮኔክሽኑ 100+ ከሆነ በሳምንታዊ ክፍያ ይከራይልዎታል።
በቴሌግራም t.me/ @Eth_Ortho ወይም +251716735450 አናግሩኝ። ያለ ሥራ የተቀመጠ አካውንትዎን ገቢ ያግኙበት!

Reply
Dawit Degfe Shikur August 26, 2025 - 10:24 am

ማትረፍ ብቻ ነው እንዴ እቅዳችሁ ለደንበኛው የሚያረካ አገልግሎት ለማቅረብ ትጉ

Reply
Aweloromo Kasim August 26, 2025 - 10:28 am

Endaza ka hone hulm tatakami enternet ba natsa matakm alabat

Reply
አባ ቃኘው August 26, 2025 - 10:28 am

እረ እባካችሁ tele share ብላችሁ ገንዘባችንን አውጥተን እስካሁን ምንም ነገር የለም 9ወር ሙሉ ። ወይም ደግሞ ገንዘባችንን መልሱ ። #ethio telecom

Reply

Leave a Comment