banner

ቅዱስ ኮምፕሌክስ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል

#FastMereja I የቅዱስ ሪዞርትና ሆቴሎች ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አካል የሆነውና 18 ወለል ያለው ግዙፉ ቅዱስ ኮሞፕሌክስ ተመርቆ ወደስራ ገብቷል።

ኮምፕሌክሱ በበርካታ ዘርፎች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ዲዛይን ተደርጎ የተሰራ ቅይጥ ኮምፕሌክስ ሲሆን እጅግ ደረጃውን የጠበቀና በጥራት የተሰራ ስለመሆኑ በምርቃቱ ዕለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮናስ ተስፋዬ እንዲሁም አጠቃላይ የኮምፕሌክሱን ምርቃትና የድርጅቱን ሁኔታ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ስራ አስኪያጇ ኢየሩሳሌም ወንዶሰንና የድርጅቱ የቦርድ አባልና ሒሳብ ሹም አቶ ዘላለም አብዬ ተናግረዋል።

ቅዱስ ኮምፕሌክስ ኡራኤል አደባባይ ወደ እስጢፋኖስ መሔጃ በዋናው አስፓልት ላይዐይን በሆነ ቦታ የሚገኝ ግዙፍና ዘመናዊ ኮምፕሌክስ ሲሆን በውስጡም በ1ኛና በ2ኛ ወለል ላይ 120 ሱቆት፣በሶስተኛና አራተኛ ወለል ላይ26 ያህል ለባንክ ለኢንሹራንስ ለፈርኒቸርና ለተለያዩ የንግድ ማሳያ ሱቆች እንዲሁም 420 ካ ሜ ላይ ያረፈ ለግዙፍ ሬስቶራንት አገልግሎት የሚውልና ሌሎችንም አገልግሎቶችንያካተተ ነው።

ኮምፕሌክሱን አሁን እስካለበት ጀረጃ ለማድረስ ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ሲሆን ለባንክ ዋስትና በተደረገ የባንኮች ግምት 1.7 ቢሊዮን ብር እንደሚያወጣ ተመን ወጥቶለታል። ኮሞፕሌክሱ ከዚህም በተጨማሪ ከአምስተኛ እስከ 8ኛ ፎቅ ድረስ ከ60 በላይ ቢሮዎች ፣ ከዘጠነኛ እስከ14ኛ ፎቅ ድረስ 48 ቅንጡ የመኖሪያ አፓርታማዎች፣ 15ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ1350 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ለጋዜቦ ፣ለሳውናና ስቲም አገልግሎት የሚውል ሰፊ ቦን ያካተተ ሲሆን በኮምፕሌክሱ አንደር ግራውንድ በተገነባው ባለሁለት ወለል የመኪና ማቆሚያ በአንድ ጊዜ ከ90 በላይ መኪኖችን እንደሚያስተናግድ አቶ ዮናስ ተስፋዬ በምርቃቱ ዕለት ባደረጉት ንግግር አብራርተዋል። ኮምፕሌክሱ ብዙ ውጣውረዶችን አሳልፎ በአባላቱ ቁርጠኝነትና በቦርድ አመራሮቹ ብቃት ለውጤት የበቃ ሲሆን እስካሁን ለህንፃው ግንባታ ከባንክ የተወሰደው ብድር 50 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑንና ሌላው ወጪ በአክሲዮን አባላቱ አቅም የተሸፈነ ስለመሆኑም ለማወቅ ተችሏል።

ቅዱስ ሪዞርትና ሆቴሎች ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተለያየ የንግድና ኢንቨስትመንት ስራ ላይ በተሰማሩና የካበተ ልምድ ባላቸው 46 ዓባላት የተመሰረተ ሲሆን በሆቴልና ሆስፒታሊቲ፣ በሪል ስቴት አልሚነት፣ በሪዞርቶችና በቱሪዝም ዘርፍ ለመሰማራት ራዕይ ሰንቆ የተመሰረተ ሲሆን የመጀመሪና የበኩር የሆነውን ግዙፉን ቅዱስ ኮምፕሌክስን እውን በማድረግ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ሰሞን በድምቀት አስመርቆ ጉዞውን ጀምሯል ሲሉ የቦርድ አባሉና የሒሳብ ሺሙ አቶ ዘላለም አብዬ ተናግረዋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ላይ የሚገኘው ቅዱስ ኮምፕሌክስ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ከመሆኑም በላይ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥርና በተጨማሪ በአገር ኢኮኖሚ ላይም የበኩሉን ጉልህ አስተዋፅኦ እንደማያበረክት የገለፁት በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘመን ተስፋዬ ቅዱስ ሪዞርትና ሆቴሎች በቀጣይ በክፎለከተማችን ለሚሰራቸው ማንኛዎም የልማት ስራዎች ከጎናቸው እንቆማለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት በክፍለከተማው የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ናሆም መንግስቱ፣ የወረዳ 8 ምክትል ስራ አስፈፃሚ የወሰን አመንቴ የቂርቆስ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሐላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ሲሆኑ በክፍለ ከተማቸውና በወረዳቸው የተገነባውን ይህን ግዙፍ ቅይጥ ኮምፕሌክስ አድንቀው ለባለአክሲዮነኖቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል። በቀጣይ የድርጅቱ ጉዞም ከጎናቸው በመሆን ትብብር እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የቅዱስ ሪዞርትና ሆቴሎች ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስካያጅ ኢየሩሳሌም ወንዶሰን በበኩላቸው ይሄ ጅምር መሆኑንና በቀጣይ ትልልቅና ትርጉም ያላቸው ኢንቨስተመንቶችን ለመከወን ራዕይ ሰንቆ የተነሳ ተቋም ስለመሆኑ አብራርተዋል። በተለያየ የንግድ ስራ የተሰማሩ ነጋዴዎች ወደቅዱስኮምፕሌክስ መጥተው እንዲጎበኙ እንዲነግዱና እንዲያተርፉ ብሎም በቅንጡ አፓርታማዎች ላይ የመኖር ሕልማቸውን እንዲያሳኩ ስራ አስኪያጇ ጥሪ አቅርበዋል።

#ቢዝነስ





Leave a Comment