banner

አገልግል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማኀበር ለ1 ወር የሚቆይ የብድር ፓኬጆችን ይፋ አደረገ

#FastMereja I አገልግል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማኀበር አዲሱን ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ፓኬጆችን ይዞ መምጣቱን በዛሬዉ እለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ከመስከረም 6 እስከ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ለ1 ወር የሚቆይ የተለያዩ ፓኬጆችን ይዞ መምጣቱን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አለሙ ፀጋዬ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

በዚህ 1 ወር ውስጥ 50 እና 60 ሰዎችን 1ዐዐ ሚሊየን ብር አበድረው ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዳቸዉንም ገልፀዋል።

1 ወር በሚቆየው ፓኬጅ ውስጥ የመኪና ባትሪ ብድር 25% የቆጠበ ፣ የማሽነሪ ብድር ፣ የመኪና ብድር 30% የቆጠበ የመሳሰሉት ሲሆኑ 30% ቅናሽ ያለባቸው ፓኬጆችም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ድርጅቱ በ1 ሰራተኛ በ26 ሺ ብር ካፒታል ከ3 አመት በፊት እንደተመሰረተና ከ26 ሺ ብር ካፒታል የተጀመረዉ ይህ የቁጠባ ማህበር አሁን 3ዐዐ ሚሊየን ብር በላይ በመድረስ ለብዙዎች ብድር መሥጠት መቻሉን ገልፀዋል።

#ቢዝነስ





1 comment

Log Out September 16, 2025 - 10:11 am

እርግጠኛ ነክ በ26k መነሻ ነው የጀመረው?

Reply

Leave a Comment