#FastMereja I ጊፍት ሪል ስቴት ለአዲስ ዓመት ሁለተው ኤክስፖ 1 ሺህ 500 ቤቶች ሽያጭ ይፋ አደርጓል፡፡ በሽያጭ ኤክስፖው አዳዲስ ፕሮጀክቶችም ለህዝብ በይፋ ተዋውቀዋል፡፡
ጊፍት ሪል ስቴት፣ ሦስት መንደሮችን ጨርሶ ለህብረተሰቡ ባስረከበበት ማግስት፣ አራተኛውን የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር፣ “የዋና ከተማችን ዋና ከተማ” በሆነው በለገሃር ላይ 4ሺህ ቤቶችን በጥራት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ መንደር “መኖር በጊፍት መንደር” በሚል መሪ ቃል፣ የሽያጭ ኤክስፖ፣ ከመስከረም 29 – ጥቅምት 8/ 2018 ዓ.ም. ያካሂዳል፡፡
በኤክስፖው በ2% ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት መሆን የሚቻል ሲሆን፣ እስከ 25% ልዩ ቅናሽ ተደርጓል፡፡
በዛሬው ዕለት በመዲናዋ ግንባታ የጀመሩና በቀጣይ የሚገነቡ አዳዲስ ፕሮጀክቶችም ለህዝብ ይፋ ተደርገዋል፡፡
ከነዚህ መካከል የ12 ሺህ ቤቶች ማስፋፊያ አካል የሆኑ በሁለተኛና ሶስተኛ ዙሮች የሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች፣ እንዲሁም በ6 ኪሎ፣ በቦሌ መድሃኒዓለም፣ በፊጋ፣ በ22 ማዞሪያ፣ በተክለሃይማኖት፣ በሲኤምሲ እና በሌሎች አካባቢዎች 4 ሺህ፤ በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ ቤቶች ተዋውቀዋል፡፡
ለኑሮ ምቹ በሆኑት መንደሮቻችን፣ ትምህርት ቤ/ቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ተካተዋል፡፡
ጊፍት ሪል ስቴት፣ እስካሁን፣ በ165 ሺህ ካሬሜትር ላይ በሲኤምሲ እና ፈረስ ቤት ሦስት ትላልቅ መንደሮችን ገንብቶ ለማኅበረሰቡ አስረክበዋል።
#ቢዝነስ




