0
#FastMereja I አሽሊ ወርልድ ቴኳንዶ ክለብ ለአንድ ዓመት በተለያየ ዳን ያሰለጠናቸዉን ሰልጣኞች አራት ኪሎ በሚገኘዉ ራስ አምባ ሆቴል አስመርቋል።
በኢንተርናሽናል ማስተር ኤዶኒያስ ጌቱ አሰልጣኝነት ስልጠናዉ የሚሰጥ ሲሆን፣ በዕለቱ የሰልጣኝ ወላጆች እና ግራንድ ማሰተሮች እንዲሁም ታዉቂ ግለሰቦች እና ተጋብዥ እንግዶች በተገኙበት የአመቱን ሰልጣኞች አስመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአለም አቀፉ የጂቲቲ ኤፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና በኢትዮጵያ ተጠሪ ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ (ዶ/ር) በመገኘት ተመራቂ ሰልጣኞችን አበረታቷል።
አሽሊ ወርልድ ቴኳንዶ ክለብ ከአሰለጠናቸዉ ሰልጣኞች መካከል በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደሩ የቴክዋንዶ ተወዳዳሪዎችን ማስመረጥ የቻለ ሲሆን በኮሪያ የትምህርት ስልጠና ማግኘት የቻሉ ታዳጊዎችንም አስመርቋል።
ኢትዮ ያሬዳዊ ባህላዊ የዉዝዋዜ ቡድን የመድረኩ ድምቀት መሆን ሲችል፣ የስልጠና ክለቡን ለማጠናከርም የጨረታ ስነ-ስርዓት ተከናዉኗል።
አሽሊ ወርልድ ቴኳንዶ ማሰልጠኛ ክለብ በ2010 ዓ.ም ምስረታዉን ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለ8ኛ ዙር ሰልጣኞችን ማስመረቅ ችሏል።
#ስፖርት




