banner

ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ አዳዲስ የጤና እና ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

#FastMereja I ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ (EDF) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የፒላቲስ ሪፎርመር ስቱዲዮን በማስተዋወቅ የፊትነስ ዘርፉን ወደ አዲስ ደረጃ አሸጋገረ።

የአካል ብቃት አሰልጣኝ ቶማስ ኃይሉ (የEDF ባለቤት) የሰውነት ጥንካሬን፣ መተጣጠፍንና አቋምን ለማስተካከል የሚረዳው ይህ ስቱዲዮ፤ በተለይም ለጀርባ ህመም ማገገሚያ እና ለሰውነት ቅርጽ እጅግ ውጤታማ እንደሆነ ተናግሯል።

ተቋሙ ከወበራ ሶልዩሽንስ ጋር በመተባበር በቅርቡ ይፋ የሚያደርገው የ“EthioFit” መተግበሪያ የቤት ውስጥ ስልጠናን፣ የሀገር ውስጥ የምግብ እቅድን እና በAI የተደገፈ ክትትልን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ እነዚህን ዘመናዊ አሰራሮችና ሳይንሳዊ ግኝቶች በማቀናጀት፣ የማህበረሰቡን የጤና አኗኗር ዘይቤ ለመቀየር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። አዲሱ የEthioFit መተግበሪያ በቅርቡ በPlay Store እና App Store ላይ ለተጠቃሚዎች ክፍት ይሆናል።

የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜ ከፊትነስ ጋር በማጣመር ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ቁርጠኛ የሆነው ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ፤ አዳዲስ አገልግሎቶቹን በቅርቡ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንደሚያደርግ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

#ስፖርት #ቢዝነስ መረጃ





Leave a Comment