banner

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በትግራይና አማራ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲታገድ አዘዘ

#FastMereja I የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አወዛጋቢ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ በጊዜያዊነት እንዲታገድ ትእዛዝ ሰጠ።

​ፍርድ ቤቱ ይህንን ትእዛዝ ያስተላለፈው የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የተባለው ፓርቲ ተወካይ አቶ ጌታቸው ረዳ ካቀረቡት አቤቱታ በኋላ ነው።

​ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ምርጫ ቦርድ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል አወዛጋቢ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ክርክሩ ታይቶ እስኪያልቅ ድረስ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 መሠረት ታግዶ እንዲቆይ ታዟል።

​ከሳሽ ያቀረበው ክስና ማስረጃ ለተከሳሽ (ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ) እንዲደርሰውና ተከሳሹ ለየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት መልሱን ይዞ እንዲቀርብ ታዟል።

#ፖለቲካ መረጃ

Leave a Comment