banner

ዶንኪ ድራይቭ የሜትር ታክሲ ፕላትፎርም ይፋ ሆነ!

#FastMereja I ዶንኪ ድራይቭ የሜትር ታክሲ መተግበሪያ ፕላትፎርም በዛሬዉ እለት ታህሳስ 7/2018ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።

ዶንኪ ድራይቭ በሃሴት ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ስር የተዋቀረ ሆኖ የትራንስፖርት አገልግሎቱን በተለይም በአሽከርካሪውና በተገልጋዩ መካከል ያለውን አገልግሎት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያሳልጥ ወጥ መተግበሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ፕላትፎርም በልዩነት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሜትር ታክሲ አገልግሎት እንደሆነም ተገልጿል።

ዶንኪ ድራይቭ የሜትር ታክሲ አገልግሎት በሁሉም የኑሮ ደረጃ ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያረግ እንደሆነም ተነግሯል።

ይህ የሜትር ታክሲ ለየት የሚያደርገዉ የጉዞ ማስጀመሪያዎችን እራሱ ተሳፋሪዉ ማስጀመር እንደሚችል ይህም በዋጋ ታሪፍ ላይ መጭበርበሮች እንዳይኖሩ የሚያደርግ እና የጉዞ ክፍያዎችን በተለያዩ ዲጂታል የክፍያ አገልግሎት መገልገል የሚያስችል በመሆኑ ነዉ።

ከዚህም ባሻገር ተሳፋሪዉ ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችሉ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙት ዶንኪይ ድራይቭ በሌላ ወገን ክፍያዉ በቀጥታ እንዲፈጸምለት ማድረግ የሚያስችል መተግበሪ እዉን አድርጎ በሥራ ላይ አዉሏል ።

ሌላው በጣም ልዩ የሚያደርገው ነገር ከኦሮሚያ ባንክጋር በመተባበር አሽከርካሪዎች ከ5 ሺህ እስክ 50 ሺህ ብር ድረስ ያለምንም ተያዥና ወለድ ብድር እንዲያገኙ የሚስችላቸዉን አሰራር በመዘርጋቱ አሽከርካሪዎች ለሚገጥማቸዉ የመለዋወጫ፣ የነዳጅ እና ሌሎች አስቸኳይ የገንዘብ እጥረት ፈጣን የመፍትሄ አማራጭ ያዘጋጀላቸዉ መሆኑ ተገልጿል።

#ቢዝነስ ዘገባ





Leave a Comment