banner

ኦክሎክ ሞተርስ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማሳያ እና የጥገና ማዕከል አስመረቀ!

#Fastmereja: በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ላለፉት 20 ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየው ኦክሎክ ሞተርስ በአዲስ አበባ ለኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ማሳያ ክፍል (Show Room) እና የጥገና ማዕከል በዛሬዉ እለት አስመርቋል።

ተቋሙ መንግስት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን አጠቃቀም ለማበረታታት ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ፤ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሰባት ዓይነት የ“ውሊንግ” (Wuling) የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ገጣጥሞ ለገበያ ማቅረቡን ገልጿል።

እነዚህ ተሸከርካሪዎች ከ5 እስከ 14 ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ያላቸውና ለግልም ሆነ ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አዲሱ የጥገና ማዕከል በዘመናዊ ማሽነሪዎችና በሰለጠኑ ባለሙያዎች የተደራጀ ሲሆን፣ ዓላማውም ተሽከርካሪዎችን ገጣጥሞ ከመሸጥ ባለፈ ከሽያጭ በኋላ የሚመጣውን የጥገና ፍላጎት በብቃት ለማርካት መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።

ማዕከሉ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ ተብለው የተዘጋጁ ልዩ መሣሪያዎች ያሉት በመሆኑ፣ በዘርፉ የሚታየውን የጥገና ማዕከላት እጥረት ለመቅረፍ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ኦክሎክ ሞተርስ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ አሻንዛ ታክሲዎችን በማስተዋወቅና በቱሪስት ትራንስፖርት ዘርፍ ዘመናዊ የውሊንግ ተሸከርካሪዎችን በማቅረብ የሚታወቅ ሀገርበቀል ድርጅት ነው።

በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቢዝነስ መረጃ





Leave a Comment