banner

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን አስመረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መጠነ ሰፊ ርዕይ ያላቸው የህክምና አገልግሎቶች ለመስጠት እንደተገነባ ገልጸው ገና ብዙ ርምጃ መራመድ ቢጠበቅብንም በጤናው ዘርፍ በቂ የህክምና አገልግሎት ለዜጎቻችን ለማቅረብ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለዜጎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በማቅረብ ሥራ ለሚተጉ የጤና ባለሞያዎችና ሰራተኞች ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡ የጤና ሥርዓታችንን ለማዘመን በምናደርገው ያላሰለሰ ጥረት ቀጣይ አስተዋጿቸው እና አገልግሎታቸው እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል:: ለሆስፒታሉ ግንባታ 1.4 ቢሊዮን ብር ወጪ የወጣበት እና 600 ደረጃቸውን የጠበቁ አልጋዎች ያሉት ሲሆን እጅግ ዘመናዊ የተባሉ የሕክምና መስጫና የምርምራ ቴክኖሎጂዎችም አሉት። ሆስፒታሉ የአካባቢውና የአጎራባች ክልሎች፣ ዞኖች ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

Leave a Comment