banner

6 ሚሊዮን ብር የወጣበት የቬሮኒካ አዳነ መጠሪያዬ አዲስ አልበም ሊወጣ ነው።

የድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ “መጠሪያዬ” የተሰኘ አዲስ አልበም ተጠናቆ ለአድማጭ ሊደርስ እንደሆነ ዛሬ ነሃሴ 13/2016 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

መጠሪያዬ አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ 3 አመት የፈጀ ሲሆን 12 ሙዚቃዎች በውስጡ አሉት፣ 4 ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ፣ አቡዲ 7 ሙዚቃ፣ ሱራፌል የሺጥላ 1 ሙዚቃ በግጥም እና ዜማ ተሳትፏል።

ታምሩ አማረ፣ አዲስ ፍቃዱ፣ አብርሃም ኪዳኔ፣ ሮቤል እንዳለ በሙዚቃ ቅንብር ተሳትፏል፣ ሰለሞን ሀ/ማርያም ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሰርቶታል።

አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች በአሜሪካ አትላንታ ተስርተዋል፡፡ አልበሙ ስለፍቅር፣ ስለሰላም፤ ስለሀገር፣ ስለተስፋ፣ ስለምስጋና እና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል፡፡

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ አለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ ጋር በ160,000 ዶላር በመላው አለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል። በኢትዮጵያ ብር 17 ሚሊየን ብር አከባቢ ነው።

መጠሪያዬ አልበም የፊታችን ነሀሴ 17 እንደሚለቀቅ ቢገለፅም በታዳጊ ሔቨን ፍትህ ጥያቄ ምክንያት ወደ ነሃሴ 23/2016 ዓ.ም ቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንዲሁም በቴሌግራም ካሴት የሙዚቃ መተግበሪያ ላይ ይለቀቃል።

በህፃን ሔቨን ላይ የደረሰውን ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አውግዛለች፣ ለሔቨን እናቷም መፅናናትን ተመኝታለች።

Leave a Comment