banner

አማራ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት 377 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተገለፀ።

አማራ ባንክ በተጠናቀቀው የ2023/24 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 377.2 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተገለፀ። ዛሬ ነሃሴ 13/2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠ መግለጫ አማራ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 25.1 ቢሊየን መድረሱም ተገልጻል።

ባንኩ የተሰበሰበውን ተቀማጭ ገንዘብ የፋይናንስ ተደራሽነትንና አካታችነትን ባማከለ አሰራር ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አጠቃላይ ብር 20.3 ቢሊየን ብድር መስጠቱ ተነግሯል።

ባንኩ በአራቱም የአገሪቱ ማዕዘናት ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት 311 ያደረሰ ሲሆን የደንበኞች ብዛትም ከ1.8 ሚሊየን በላይ ለመሆን ችሏል።

ባንኩ 571 ሺ በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን እንዲሁም ከ50ሺ በላይ የካርድ ተገልጋዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን በርካታ የኤቲኤም እና የፖስ ማሽኖችን በተለያዩ ቦታዎች በማኖር በዲጂታል ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ከተለያዩ ፊንቴኮች ጋር መስተጋብር በመፍጠርና አብሮ በመስራት የክፍያ ስርዓቱን ምቹ እና ቀላል በማድረግ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

Leave a Comment