banner

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር በደስታ እንደምትቀበል ገለፀች

#FastMereja I ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር በደስታ እንደምትቀበል አስታወቀች። ይህ አወቃቀር የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ አሜሪካ ገበያ ሲገቡ የሚጣልባቸውን ታሪፍ 10% ብቻ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳድጋል ብሏል።

መንግስት ይህ ውሳኔ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና የኢትዮጵያን ኤክስፖርት ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዉሳኔዉን ተከትሎ እንዳስታወቀዉ ይህ አዲሱ የታሪፍ አወቃቀር ኢትዮጵያ እንደ ቬትናምና ባንግላዴሽ ካሉ ትልልቅ የማምረቻ ማዕከላት ጋር ስትወዳደር የተሻለ እድል እንዲኖራት ያደርጋል።

“የ10% የታሪፍ መጠን ለኢትዮጵያ ላኪዎች ከፍተኛ ማበረታቻ ይሰጣል” ሲል ሚኒስትሩ አስታውቋል ። “ይህ የኢትዮጵያ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ ተወዳዳሪ ዋጋ እንዲኖራቸው በማድረግ የፍላጎት እና የኢንቨስትመንት መጨመርን ያመጣል ሲል ተስፋዉን ጥሏል
።

ይሁን እንጂ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፣ ይህንን እድል በአግባቡ ለመጠቀም ኢትዮጵያ አሁንም በርካታ ተግዳሮቶችን መወጣት አለባት። የመሠረተ ልማት ውስንነት፣ የምርት ጥራት እና ደረጃዎች፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ጥቂቶቹ መሆናቸውን አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

Via: Capital
#ቢዝነስ

10 comments

Tez Tezuka April 3, 2025 - 9:27 am

ግን እራሷን እንዴት ብታይ ነዉ!?🙄

Reply
ጃል ጫላ April 3, 2025 - 9:27 am

በጣም ነው እንዴ ደስ ያላት

Reply
Tariku Asmamaw April 3, 2025 - 9:30 am

ወዳ ነው የምትቀበል😂

Reply
Jawi Fira Oromoo April 3, 2025 - 9:30 am

የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ይላል የሀገሬ ሰው ለ ብልግና የዋጋ ጭማሪ, የኑሮ ዉድነት, የ ዋጋ ግሽበት, የዜጎች ደህንነት አያሳስበዉም የብልግና ደሴት ወንበርብቻ አይነካ እንጂ ሌላው ጉዳይ አይደለም

Reply
Sami Sisay April 3, 2025 - 9:31 am

ምንልከው አለን እንዴ ብዙ ጊዜ ሰው ሲሄድ ማየው

Reply
C'he Gu Evara April 3, 2025 - 9:31 am

10% ታሪፍ ተጥሎባት ነው እንዴ በደስታ የምትቀበለው 🙆‍♂️🙆‍♂️🙆‍♂️

Reply
Yosef Mulusew April 3, 2025 - 9:32 am

😂😂😂😂ባትቀበልስ

Reply
Asfaw Mengesha April 3, 2025 - 9:32 am

Batekebelsi?

Reply
Kiyaa Deraa April 3, 2025 - 9:32 am

እነ ሌላ ምን አማራጭ አለት ከመቀበል ውጪ

Reply
Xv Åmexø April 3, 2025 - 9:32 am

አልቀበልም ብትልስ የት ልትሄድ ምን ልታመጣ

Reply

Leave a Comment