📌 የማርኬቲንግና የማስታወቂያ ባለሙያ ሞዴል ሊዲያና ሰለሞንን የድርጅቱ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል፡፡
#FastMereja I የሂዩማን ሄርና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን በማስመጣት የሚታወቀው ዞማ ሄር አሁን ደግሞ የውበት አጠባበቅ ሙያ ስልጠናን ለመስጠት ዞማ የውበት ማሰልጠኛ በሚል ስያሜ ቦሌ ብራስ ሪያለቲ ፕላዛ ህንፃ ላይ የስልጠና ማዕከል ከፍቷል፡፡
ዞማ የውበት ማሰልጠኛ በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድና ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን፤ ጥራት ካላቸውና ዘመኑ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ የእድገት ደረጃ ከሚያሞሉ የስልጠና መሳሪያዎች ጋር መከፈቱን የድርጅቱ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ አርአያ ሐጎስ ገልፀዋል፡፡
የስልጠና ማዕከሉ እውቅና ባገኘባቸው የሜካፕ፣ የፌሻል፣ የጥፍር እና የፀጉር ስራ እንዲሁም የአይላሽ እና የኦምብሬ የሙያ ዘርፎች ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን የድርጅቱን አላማና የስራ ክንውን ወደ ህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ የማርኬቲንግና የማስታወቂያ ባለሙያ ሞዴል ሊዲያና ሰለሞንን የድርጅቱ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል፡፡
አርቲስት ሊዲያና ባላት ጠንካራ የስራ ባህል፤ በመልካም ስነ ምግባርና፤ በከፍተኛ ጥረት እራሷን ለስኬት በማብቃት ለሴቶችና ወጣቶች መልካም አርአያ በመሆኗ እንደመረጧት ገልጿል።
በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎትና ራዕይ ኖሯቸው በፋይናንስ እጥረት ምክንያት መማር ያልቻሉ ሰልጣኞችን ለማገዝ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመነጋገር በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ የዱቤ አገልግሎት አግኝተው የሚማሩበትን እድል መመቻቸቱ ተነግሯል።
#ቢዝነስ




