banner

ፋሲካ በሚሊኒየም ባዛር እና ኤክስፖ

#FastMereja I የ2017 ዓም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አስመጪዎች እና አምራቾች ከሸማች ሕብረተሰቡ ክፍል ጋር እየተዝናና የሚገበያይበት “” ከመጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በታላቁ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

በዚህም የፋሲካ ባዛር እና ኤክስፖ ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል በአልን ምክንያት አድርጎ ከሚገጥመው የዋጋ ንረት በተመጣጣኝ እና በቅናሽ ዋጋ ከራሱ ከአምራቹና ከአስመጪው የሚገበያይበት እንደሆነ ነው የተነገረው።

ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የመዝናኛ፣ የምግብ እና የመጠጥ ፕሮግራሞች የሚገኙበት ባዛር እና ኤክስፖ መሆኑ ተገልጿል።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጠናት፣ ሚኒስትሮች፣ ባለሀብቶች፣ የሚዲያ ባለሙያ እና ተዋቂ ሰዎች በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

በዝግጅቱም ላይ አልባሳት፣ የስጦታ እቃዎች፤ አቅራቢና አስመጪ፣ የምግብና መጠጥ፤ ሽጮች የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት ሲሆን በአጠቃላይ ከ2,000 በላይ አስመጪና ሻጮች ይሳተፉበታል በዚህም ዝግጅት በቀን ከሰባት ሺህ እስከ አስር ሺህ ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በየቀኑ ለሀገራችን የሚገኙ ባህላዊ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ባለሙያዎች በየቀኑ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በተወዳጅ ባንዶቻቸው በመታጀብ እንደሚያቀርቡ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

#ቢዝነስ





1 comment

Yohannis Tamire April 4, 2025 - 1:50 pm

መልካም ፈሲካ

Reply

Leave a Comment