banner

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዲጂታል ሎተሪ ይፋ ሆነ

#FastMereja I በኢትዮጵያ የመጀመርያው የሆነውና ታሪካዊው የዲጅታል ሎተሪ መጀመር ማብሰሪያ ሥነ ስርአት ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተካሄደ፡፡

ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ሀብታሙ ሃ/ሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤዛ ግርማና የታምኮን ሶፍትዌር ሶሉይሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ከበረ በዚሁ ሥነስርአት የዲጅታል ሎተሪውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤዛ ግርማ በመክፈቻው ሥነስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በአሁኑ ወቀት በተለየ ተቋማዊ የለውጥ ጎዳና ላይ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ለውጦች መሃል ሎተሪዎቹን በዲጅታል ማዘመን መሆኑን ጠቅሰው ይህ መሰረታው ለውጥ የሎተሪዎችን ተደራሽነትን በማስፋፋት የገበያ ድርሻን ከማሳደጉ በላይ እንደሃገር የተያዘውን የዲጅታላዜሽን ጉዞ እውን ለማድረግ የራሱን አስተዋጾ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በዚሁ ንግግራቸው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የዲጅታል ሎተሪ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ሲያደርግ፣ ደንበኞቻችን በቀላሉ የሚጫወቱት፣ ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆነውን የዲጂታል ሎተሪ የመሰረተ ልማት ችግሮችና ጊዜ ሳያግዱት በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ደንበኞቻችን በቀላሉ ተደራሽ ይሆናል ብለዋል።

የዲጅታል ሎተሪ በመጀመሪያው ምእራፍ ከዚህ ቀደም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታወቁትን መውጫ ጊዜያቸው የተወሰነላቸው ወረቀት እና የሚፋቁ የፈጣንና ቢንጎ ሎተሪዎች በዲጅታል መልክ በተለያዩ ቋንቋዎች በማዘጋጀት የሚያቀርብ ሲሆን በቀጣይ ምእራፍ በተለያየ አይነት ዘመኑን የዋጁ አዝናኝ የሎተሪ ጨዋታዎችን የሚጨምር ሲሆን ይህም አሁን በገበያ ላይ ካሉት ከወረቀት ሎተሪዎች በተጨማሪ ጎን ለጎን በድረገጽ ፣ በሞባይል አፕሊኬሽን ፣በኤስ ኤም ኤስ እንዲሁም ዘመን እና ቴክኖሎጂ በሚፈቅዳቸው መንገዶች አማካኝነት ሎተሪዎችን በማቅረብ ህብረተሰቡ ዕድሉን የሚሞክርበትና የሚሸለምበት ይሆናል፡፡

በመጨረሻም ድርጅታቸው በሁሉም አማራጮች የቀረበው ይህ የዲጂታል ሎተሪ አገልግሎት በእጅ ስልክ፣ በኮምፒዩተር፣ በአጭር የጽሁፍ መለእክት፣ በዩ ኤስ ኤሲ ሲዲ፣ ስካን አድርጎ በመጫዎት፣ ስልክ ደዉሎ በመጫወት፣ ከእድል አዟሪዎች በፖስ ማሽን በመግዛት እንዲሁም በሌሎች ሃገሮች እንደተለመደው በተለያዩ ሱቆች አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቱ ማጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡

#ሳይ_ቴክ





Leave a Comment