#FastMereja I የፓኪስታን መንግሥት፤ በንግድ ሚኒስቴር፣ በፓኪስታን የንግድ ልማት ባለሥልጣን እንዲሁም በአዲስ አበባ በሚገኘው የፓኪስታን ኤምባሲ የንግድ ዘርፉ አማካኝነት 5ኛውን የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባዔ እና “በፓኪስታን የተመረተ” ኤግዚቢሽን ሊያዘጋጅ መሆኑ ተገለጠ።
ዛሬ ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ከ100 በላይ ከፍተኛ የፓኪስታን ኤግዚቢሽን አቅራቢዎች ከተለያዩ ዘርፎች ማለትም ከጨርቃጨርቅ፣ ከመድኃኒት፣ ከኢንጂነሪንግ፣ ከምግብና አግሮ ፕሮሰሲንግ ውጤቶች፣ ከቆዳ ውጤቶች፣ ከግንባታ ዕቃዎች፣ ከመዋቢያዎች እና ከጤና እንክብካቤ ዘርፎች የተውጣጡ የፈጠራ ምርቶቻቸውን እና የወጪ ንግድ አቅማቸውን ያሳያሉ ተብሏል።
ከግንቦት 7-9/2025 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን ታዋቂ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች እና የንግድ መሪዎች ከፓኪስታንና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመገኘት የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነቶችን ለማሳደግና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማምጣት በሚቻልበት ስልቶች ላይ ይመከራሉ ተብሏል።
ኤግዚቢሽኑ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ ለንግድ ለንግድ (B2B) ግንኙነቶች ተለዋዋጭ መድረከ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ይህም የፓኪስታን ኤግዚቢሽን አቅራቢዎችና የአፍሪካ ገዢዎች የንግድ ዕድሎችን እንዲቃኙና ትርጉም ያለው አጋርነት እንዲመሰርቱ ያስችላቸዋል።
የግንኙነት መረብ መፍጠር ዕድሎች፣ ከኡጋንዳ፣ ከጅቡቲ፣ ከኬንያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሩዋንዳ፣ ከቡሩንዲ፣ ከናይጄሪያ፣ ከጋና፣ ከሶማሊያ እና ከታንዛኒያ የተውጣጡ ልዑካን ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ሰፊ የግንኙነት መረቦችን ለመፍጠርና ለወደፊት የንግድ ስምምነቶች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተገልጿል።
#ቢዝነስ





2 comments
መንግስታቸዉ ከህንድ ጋር ጦርነት እነደገጠመ አውቀው ይሆን ?
በስበቡ ለጦርነታቸው ወጣት አዋጡልን እንዳይሉን ብቻ