banner

ጃኳር ግሩፕ በአዲስ እና ዘመናዊ ፈጠራዎች የተሞላውን የባኞ ቤት እና የመብራት ውጤቶቹን ማሳያ አስመረቀ

#FastMereja I የባኞ ቤት እና የመብራት ውጤቶችን አቅራቢ የሆነው ጃኳር ግሩፕ ዘመናዊ ውጤቶቹን የሚያሳይበትን ቦታ ዛሬ ግንቦት 28/2017 ዓ.ም በይፋ ከፍቶ አስመረቀ።

በአዲስ አበባ ካዛንቺስ ጆበርግ ህንፃ ላይ መገኛውን ያደረገው ማሳያው ለኢትዮጵያ ገበያ የሚመጥኑ የተሟላ ዘመናዊ ውጤቶቹ በአንድ የሚገኙበት የገበያ ማዕከል ይሆናል ተብሏል።

“አላማችን ጥራት ያላቸው ምርቶችን ማቅረብ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ እድገት ላይ ባለሙያዋችን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በማዘመን እና የስራ እድሎችን በመፍጠር የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አጋር መሆን ጭምር ነው፡፡” ሲሉ በአፍሪካ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገሮች የቢዝነስ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሪካርዶ ሌዥ ተናግረዋል።

ጃኳር አለምአቀፍ ግሩፕ እ.ኤ.ኣ በ2017 በአዲስ አበባ በይፋ ተቋቋመ።

#ቢዝነስ





Leave a Comment