banner

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት ከግብር በፊት 22 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዘገበ።

#FastMereja I አዋሽ ባንክ የ2024/25 ሂሳብ ዓመትን በላቀ ውጤት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

አዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ ሰኔ 30፣2025 በተጠናቀቀው የ2024/25 የሂሳብ ዓመት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ዛሬ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

በመግለጫው ላይ የተነሱ ነጥቦች

📌 የቅርንጫፍ ስርጭቱን በማስፋት በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት ብቻ 52 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት በአጠቃላይ*የቅርንጫፎቹን ብዛት 989 ማድረስ ችሏል።

📌 የደንበኞች ቁጥር ከ15 ሚሊዮን በላይ ማድረሱንና በሂሳብ ዓመቱ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል፡፡

📌 በሂሳብ አመቱ በዲጂታል የተከናወነው የገንዘብ ዝውውር መጠን አንድ ትሪሊዮን ደርሷል፤ ይህም በሂሳብ ዓመቱ በባንኩ ከተከናወኑ የገንዘብ ዝውውሮች ከ76 በመቶ በላይ ድርሻ ነበረው።

📌 የትምህርት ስርዓቱን ዲጂታል ለማድረግ እየተደረገ ባለዉ ጥረትም ባንኩ 2,300 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች የአዋሽ ኢ-ስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የሃገራችን የመማር ማስተማር ሂደት በዘመናዊ አሰራር ስርዓት እንዲታገዝና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረጉም በተጨማሪ በሂሳብ አመቱ ውስጥ ከ3.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ክፍያ በዚህ መተግበሪያ ፈጽመዋል ተብሏል።

📌 ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ሂደት በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የስንዴ ዱቄት እና የምግብ ዘይት ድጋፍ አድርጓል።

📌 ለትግራይ ክልል ደግሞ በክልሉ ልማት ማህበር አማካኝነት በ10 ሚሊዮን ብር በጦርነት ለተጎዱ ት/ቤቶች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

📌 በጋሞ ጎፋ ዞን በደረሰዉ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖችም የሰባት ሚሊዮን ብር ፤

📌 ለኮሪደር ልማት በኦሮሚያ ክልል ለነቀምት ከተማ የ84 ሚሊዮን ብር እና በአማራ ክልል ለጎንደር ከተማ የ84 ሚሊዮን ብር ፤

📌 ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር አምስት ሚልዮን ብር

📌 ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ 2.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ለተለያዩ ሀገር በቀል ግብረ-ሠናይ ድርጅቶችም በተመሳሳይ መልኩ በርካታ ድጋፎችን አድርጓል።

📌 የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓላትን እና የረመዳን ጾም ወርን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ከአስር ሺህ በላይ የሚሆኑ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ከብር 120 ሚሊዮን በላይ ወጪ በማድረግ የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

📌 የሥራ ፈጠራ ክህሎት ኖሯቸው በፋይናንስ አቅርቦት ፅጥረት ችግር ምክንያት የሥራ ፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ ተግባር መቀየር ያልቻሉ ዜጎችን ለማበረታታት ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ያከናወነው የስራ ፈጠራ ውድድር ሁለተኛውን ምዕራፍ የታታሪዎቹ/ቀጠሌዋን ፕሮጀክት በስኬት አከናውኗል፡፡

በአጠቃላይ ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ውስጥ ለማህበራዊ ኃላፊነት ግዴታው ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለኅብረተሰቡ ያለዉን ወገንተኝነት አስመስክሯል ተብሏል።

📌 አዋሽ ባንክ የተቀማጭ ሂሣብ መጠኑን እ.ኤ.አ. በ2024/25 የሂሣብ ዓመት ብቻ በ100 ቢሊዮን ብር ለማሣደግ Mission 100 Billion የተባለ ዕቅድ ቀርጾ ሲንቀሣቀስ ቆይቷል። በዚህ ረገድ ለRetail ደንበኞች እና ከወለድ ነጻ (IFB) የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባንኩ ከዋናው መ/ቤት፣ ከቀጠና ጽ/ቤቶች፣ እና ከቅርንጫፎች ጋር በመተባበር በቅንጅት በመስራት በዘንደሮ ዓመት ብቻ ክብር 106 ቢሊዮን በላይ ተቀማጭ ሂሣብ በመሰብሰብ አጠቃላይ የተቀማጭ ሂሣብ መጠኑን ብር 332 ቢሊዮን ማድረስ ችሏል፡፡

ለዚህ ውጤት መገኘት ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (IFB) ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን ባንኩ ከ IFB ብቻ እ.ኤ.አ. በ2024/25 የሂሣብ ዓመት የተቀማጭ ሂሣብ መጠኑን የብር 18.5 ቢሊዮን ጭማሪ በማሣየት እ.ኤ.አ. ሰኔ 2025 መጨረሻ ላይ ብር 37.3 ቢሊዮን ማድረሱ ተገልጿል፡፡

📌 በሂሳብ ዓመቱ ብድር ከብር 16.6 ቢሊዮን በላይ የተሰጠው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለታቀፉ ከ14 ሺህ በላይ ደንበኞች ሲሆን፤ በተመሳሳይም መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በእጅጉ የሚጠቅም የተለያዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ እየሰራ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር መስመር (MESMER) በተሰኘ ፕሮግራም ወደ 12 ሺህ ለሚጠጉ ማይክሮ፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ባንኩ ከብር 1.3 ቢልዮን በላይፋይናንስ አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሁሉን አካታች እና ተደራሽ በሆነዉ አዋሽ ለሁሉ በተሰኘው የዲጂታል የብድር አገልግሎት አማካኝነት ከ301 ሺህ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ያለ ምንም ማስያዣ ከ 493 ሚሊዮን ብር በላይ በሂሳብ ዓመቱ የዲጅታል ብድር ተሰጥቷል።

በተጨማሪም በሂሳብ አመቱ የመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ (T-bill) ከ42 ቢሊዮን ብር በላይ ግዢ የፈጸመ ሲሆን በብሔራዊ ባንክ Open Market Operation (OMO) የብር 190 ቢሊዮን ተሳትፎ አድርጓል። ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችም ባንኩ በሂሳብ አመቱ ከ10.5 ቢሊዮን በላይፋይናንስ ያደረገ ሲሆን አጠቃላይ ለአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞች ፋይናንስ ያደረገው ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል።

ባንኩ ይህንን የዲጂታል ብድር አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከሳፋሪኮም ጋር ለመስራት ከሁለት ቢልዮን ብር በላይ የመደበ ሲሆን በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል። እነዚህ ከላይ የተገለጹት የብድር አይነቶች በተለይ ትኩረት የሚያደርጉት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ

ክፍል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የእነዚህን ወገኖች ህይወት ከማሻሻል አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው ሲሆን ይህም በቀጣይ ባንኩ ይበልጥ አጠናክሮ የሚቀጥልበት መሆኑ ተጠቁሟል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኮች መካከል የመበዳደር ስርአት (Inter-Bank Money Market) በዘረጋው መሰረት አዋሽ ባንክ በሂሳብ አመቱ አጠቃላይ ከብር 117 ቢሊዮን በላይ ለሌሎች ባንኮች አበድሯል።

የባንኩ ተመላሽነታቸው አጠራጣሪ የሆኑ ብድሮች ምጣኔ በሂሳብ ዓመቱ ከ 1.8 በመቶ በታች የሆነ ሲሆን ይህም ምጣኔ የብድር ጤናማነት አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከማሳየቱም በላይ ብሔራዊ ባንክካስቀመጠው የ5 በመቶ ጣራም ሆነ ባንኩ ካስቀመጠው እቅድ አንጻር እጅግ መልካም አፈጻፀም ነው።

በተያያዘም በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከብር 64 ቢሊዮን በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 28 ቢሊዮን ወይም የ77 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡

📌 በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ ያልተጣራ ትርፍ ከግብር በፊት ከብር 22 ቢሊዮን በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የብር 12 ቢሊዮን ወይም የ113 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

📌 አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመት 2024/25 ለተለያዩ የግብር ዓይነቶች በአጠቃላይ ከብር 10.8 ቢሊዮን በላይ በመክፈል ለሃገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። በሂሳብ አመቱ የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል አምና ከነበረበት የ10 ቢሊዮን ወይም የ37 በመቶ እድገት በማስመዝገብ በጁን 30፣ 2025 ከብር 37 ቢሊዮን በላይ ደርሷል።

ባንኩ በሃገራችን በካፒታል ገበያና በመዋዕለ ንዋይ ገበያ ረገድ እየተወሰዱ ያሉትን የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች እና እየተደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴዎች ተከትሎ ለባንካችን የሚሆኑትን መልካም አጋጣሚዎች (opportunities) ሁለ ለመጠቀም የInvestment Bank አቋቁሞ ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

አዋሽ ባንክ በሂሳብ ዓመቱ የተለያዩ ዕውቅናዎችን ያገኘ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነ ከግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ሽልማት (የዓለም ምርጥ ባንኮች) ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመሆን በብቸኝነት ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮች እውቅና እና ከ10 ቢሊዮን በላይ በታማኝነት ከፍተኛ ግብር በመክፈሉ ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል።

#ቢዝነስ





1 comment

Enjiyaw Abayneh July 1, 2025 - 2:52 pm

Yimechachu

Reply

Leave a Comment