#FastMereja I ኢትዮጵያውያንና የሌሎች ሀገራት ዜጎች የሚያሳትፈው “ማዕድ ተጓዥ ኤክስፖ” የተሰኘ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው። ማዕድ ተጓዥ ኤክስፖ ላይ የመጀመርያው ዙር በሆላንድ አምስተርዳም ከተለያየ ቦታ የሚሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያንና የሌሎች ሀገራት ዜጎችን በአንድ ቦታ እንዲሰባሰቡ በማድረግ እንዲዝናኑ፤ አንዲገበያዩ፤ አንዲወያዩ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ሀገራት እንደሚከናወነ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ማዕድ የኢትዮጵያ ተጓዥ ኤክስፖ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ባሉበት የዓለም ክፍል በማንቀሳቀስ ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገበት የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ የሚያከብር፤ የሚያስተዋውቅ በአንድ ቦታ በርካታ ዝግጅቶች የሚቀርብበት ነው ተብሏል።
የመጀመሪያው ተጓዥ ኤክስፖ በሆላንድ አምስተርዳም በፈረንጆቹ ኦክቶበር 9 እስከ 11/2025 የሚደረግ ይሆናል።
በዚህ ዝግጀት ላይ በተለያየ ዘርፍ በአሰመጪና ላኪነት እንዲሁም በባንክና ሪልስቴት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት ለመሳተፍ በአዲስ አበባ ፍቅር ያሸንፋል ቢሮ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
ዝግጅቱን ፒኮሎ 2 ካፌና ሬስቶራንት፣ ያምራል ሀገሬ ቲዩብ፣ ፍቅር ያሸንፋል የበጎ አድራጎት ማህበር በጋራ በመሆን እንዳዘጋጁት ተናግሯል።
#ቢዝነስ





1 comment
70% የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በጠኔ ሊደፋ ነው እነ ቀበጥዬ እንደ ሃብታም ሃገር ዜጋ ከሃገር ሃገር ምግብ ታስተዋውቃላችሁ።
እረ ፈጣሪን ፍሩ !!