#FastMereja I አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላተ/የህ/ስራ ማህበር በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዳማ ከተማ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ ካናብ ሞል 3ኛ ፎቅ ላይ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እንዲሁም የድርጅቱ አመራሮች በተገኙብት በዛሬው ዕለት የመክፈቻ መረኃ ግብር አካሂዷል፡፡
በዚሁ የመክፈቻ መረኃ ግብር ላይ አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላተ/የህ/ስራ ማህበር ከካናብ ሞተርስ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርሟል።
አሚጎስ በፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሺን ፍቃድ አግኝቶ አሁን በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ ለመሆን እየሰራ ሲገኝ በአዲስ አበባ እና በሁሉም ከተሞች ለመስፋፋት ያቀደ በመሆኑ በእሁኑ ሰዓት 8 ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ አዲስ አበባ በሁሉም ክፍለከተሞች እንዲሁም አዳማን ጨምሮ በክልል ከተሞች እየተስፋፋ ነው ተብሏል።
አሚጎስ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ለአባላቱ ዘመናዊ፣ ምቹና ቀልጣፋ የሆኑትን የኤሌትሪክ መኪኖችን ከአስመጪዎች ጋር በመነጋገር በሚያደርገው አሰራር ለአገሪቱ የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ ነው የተባለ ሲሆን የአሚጎስ አባላት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ተበድረው እንዲገዙ ማመቻቸት ብቻ ሳይሆን በቁጠባም የተሻለ አማራጮችን በማቅረብ ለራቸውም ለሌቹም ስራ ዕድል ዕንዲፈጥሩ ዕያደረገ ነው ተብሏል።
ጥር 5/ 2005 ዓ.ም የዛሬ 12 አመት በ20 ጓደኞሞች እና በ9 ሺ ብር የተመሰረተው አሚጎስ አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ፍቃድ አግኝቶ በጀመረበት 12 አመታት ውስጥ ከ20 ወደ 11ሺ አባላት በላይ ማደግ ችሏል:: ወደ 5500 በላይ ለሚሆኑ አባላቱ ደግሞ የብድር አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ የብድሩም መጠን እስካሁን ሲገመት ወደ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሲሆን አሁን ላይ የአሚጎስ ካፒታል ወደ 5 ቢሊዮን ብር እየተጠጋ ይገኛል፡፡
#ቢዝነስ




