#FastMereja I ከተቋቋመ የ6 ወር እድሜ ላይ የደረሰው ንጉስ የስፖርት ትጥቅ አምራች ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4 /2018 ዓ.ም ስራ መጀመሩን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።
በሃገር ውስጥ ትጥቅ ላይ መነሻውን ያደረገው ድርጅቱ በስፖርቱ ዘርፍ ላይ የራሱን አሻራ ለማስቀመጥ ሲል ወደዚህ ስራ እንደመጣ ገልጿል። ድርጅቱ በዋነኛነት ማልያ፣ ቁምጣ፣ ቱታ፣ ካሶትኒ እና በልምምድ ወቅት የሚለበስ አልባስ እንደሚያዘጋጅም ተያይዞ ተገልጿል፡፡
በተለይም ከፍተኛ ክፍተት ባለበት የማልያ አቅርቦት ላይ በተሻለ ዋጋ ተደራሽነቱን ከፍ ለማድረግ መምጣቱ ተገልፆ በንጉስ የስፖርት ትጥቅ አምራች ውስጥ በዋነኛነት በተለያዩ የጨርቅ ደረጃዎች ማልያ እና ቁምጣ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዋጋቸውም ተመጣጣኝ እንደሆነም የድርጅቱ መስራች ኢንጂነር ጌትነት ተስፋዬ ገልፀዋል።
በዛሬዉ እለትም ንጉስ የስፖርት ትጥቅ አምራች ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሜቄዶንያ የአረጋዉያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ተቋም እና JKS Ethiopia ጋር አብሮ ለመስራት በዛሬዉ እለት የፌርማ ስነስርዓት አድርጓል።
ንጉስ ትጥቅ አምራች ከዛሬ ጀምሮ ከምርት ሽያጭ ላይ 2% ለማህበሩ መርዳት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ከሌላ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ለመፈራረም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አያይዘዉ ገልጿል፡፡
#ቢዝነስ




