banner

ኦሮሚያ ባንክ ለ1ወር የሚቆይ ልዩ የሆነ የብድር አገልግሎት አስተዋወቀ

ኦሮሚያ ባንክ ለ1ወር የሚቆይ ልዩ የሆነ የብድር አገልግሎት አስተዋወቀ

#FastMereja I ኦሮሚያ ባንክ “ተደራሽ የብድር አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች” በሚል መሪ ቃል ለአንድ ወር የሚቆይ የሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት የገበያ ንቅናቄ በዛሬዉ እለት ጥቅምት 10/2/2018 በታላቅ ድምቀት አስጀመረ፡፡

ኦሮሚያ ባንክ ከሀገር በቀሉ ኳንተም ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ፍትሃዊ የብድር አገልግሎትን ለሁሉም ዜጎች ለማዳረስ ሚልኪ የተሰኘ ያለምንም የዋስትና ማስያዣ ብድር መስጠት የሚያስችል ዲጂታል የብድርአገልግሎት መተግበርያን ስራ ላይ አዉሎ እንደነበር ይታወቃል።
ባንኩ ይህን ዲጂታል የብድር አገልግሎት ለማስተዋወቅ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ለአንድ ወር የሚቆይ የገበያ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃ-ግብር በዛሬዉ እለት አስጀምሯል፡፡

ያለምንም የዋስትና ማስያዢያ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለው ሚልኪ ሁለገብ መተግበሪያ፥ በውስጡ 8 አይነት የተለያዩ አገልግሎቶችን የያዘ እጅግ ዘመናዊ መተግበሪያ መሆኑ ተገልጿል ።

በተለይም ሚልኪ ፉርቱ፤ በዕለት ገቢ ለሚተዳደሩ ወጣቶች እና ስራ ፈጣሪዎች፣ ሚልኪ የደሞዝ መዳረሻ ብድር፤ ሚልኪ ሀርሜ የሴቶች ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ብድር፤ ሚልኪ አሁን ይግዙ በኋላ ይክፈሉ -ለኤሌክትሮኒክስ እና የቤት ዕቃዎች ግዥ የሚውል ብድር፣ ሚልኪ አሁን ይቅዱ ፥ በኋላ ይክፈሉ – ነዳጅ ለመቅዳት የሚዉል ብድር፣ ሚልኪ እስኩል – ለትምህርት ቤት ከፍያ የሚዉል ብድር እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ትኬት እና የኢትዮ ቴሌኮም የአየር ሰዓትን ጨምሮ ለሚፈልጉት ማንኛዉም ጉዳይ ያለምንም ማስያዣ ደንበኞች ተበድረዉ ጉዳያቸዉን ካሳኩ በኋላ ሳይጨናነቁ ዘና ብለው የሚከፍሉበት አማራጮችን ባንኩ ማመቻቸቱን ገልጿል፡፡

ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ገና ስራ ከጀመረ 100 ቀናት ዉስጥ ለ75ሺ ዜጎችን ያለምንም ማስያጃ ብድር በመስጠት ተጠቃሚ በማድረግ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ አቅርቧል።

ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ጥበብ በመታጠቅ፤ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት እየታገዘ የብድር አሰጣጥ ስርአትን የሚያሳልጥ ሲሆን፤ በዋስትና እጦት ምክንያት ከፋይናንስ አቅርቦት ርቀዉ የቆዩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ እና ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኝ ባንክ መሆኑ ተገልጿል፡፡

#ቢዝነስ





1 comment

Abe Nezer Tsegaye October 21, 2025 - 12:07 pm

ዘንጡብን ምን ታንኩም ባንክም…..

Reply

Leave a Comment