#FastMereja I አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር ተደራሽነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለማስፋት በአንድ ጀምበር በአዲስ አበባ አምስት ቅርንጫፍ ቢሮዎች በመርካቶ ፣ በልደታ፣ በደምበል፣ በቱሉዲምቱ እና በሰሚት ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቁ አስመርቋል።
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቅርንጫፎችን ብዛት ወደ 17 ያሳደገ ሲሆን ፤ አዲሶቹን ጨምሮ በአዲስ አበባ 10 በክልል ከተሞች ደግሞ 7 የቅርንጫፍ ቢሮዎች መክፈቱን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም አብርሀ ተናግረዋል፡፡
አሚጎስ በ2030 በአለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ የፋይናስ ተቋም ሁኖ መገኘት አላማዉን ያደረገ ሲሆን ያለበት የእድገት ደረጃ በአሁኑ ሰዓት የአባላቱን ቁጥር 13 ሺህ ማድረሱ ተገልጿል።
እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት እንዳካበተ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ካፒታሉን 10 ቢሊዮን ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ እና ከ7ሺ በላይ ለሚሆኑ አባላቶቹ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ብድር እንደሰጠም ተገልጿል።
አሚጎስ በቅርብ ግዜያት ደግሞ በአሶሳ፣ በሀዋሳ፣ በጅማ ቢሮዎቹን ለመክፈት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፆ ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ እና በዓለም ዓቀፍ ህብረት ስራ ጥምረት ተሳታፊ ለመሆን በቅቷል።
#ቢዝነስ መረጃ




