0
#FastMereja I የትግራይ የቀድሞ የጊዜያዊ መስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአከራካሪ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ የሀገሪቱን ሰላም ይበልጥ የሚያውክ ነው ሲሉ ክርክራቸውን አቀረቡ።
ምርጫ ቦርድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ፣ አምስት አከራካሪ የምርጫ ክልሎች (ሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም አፍላ፣ ጠለምትና ራያ አላማጣ) ከትግራይ ክልል ውጪ ሆነው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ምርጫ እንዲያካሂዱ መወሰኑ ይታወቃል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤም ሆነ መነሻ የሆነውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ውሳኔ በጽኑ ተቃውመዋል።
ውሳኔዎቹ የሀገሪቱን ሰላም ይበልጥ ከማወክ እና ከማናጋት ውጭ ሌላ ፋይዳ ወይም ትርጉም ይኖራቸዋል ብለው እንደማያምኑ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በጽሁፋቸው አስፍረዋል።
#ፖለቲካ መረጃ
