banner

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ በጽኑ ተቃወመ

#FastMereja I ​የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአከራካሪ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ሕገ-መንግሥቱንና የፕሪቶሪያውን ስምምነት የጣሰ ነው ሲል በጽኑ ኮነነ።

የትግራይ ሕዝብ በከፈለው መስዋዕትነት የተገነባውን ሕገ-መንግሥታዊና ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመጣስ፣ በትግራይ ሕገ-መንግሥታዊ ወሰን ላይ አደጋ የሚጥል ውሳኔ መተላለፉን መግለጫው ገልጿል።

​የትግራይ ሕዝብ ድምፅ በሌለበትና ባልተወከለበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላለፈው ይህ ውሳኔ፣ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በግልጽ የጣሰ ነው ብሏል።

​ይህ “አደገኛ” የተባለው ውሳኔ የሚያስከተለው ዘርፈ-ብዙ መዘዝ ግምት ውስጥ ገብቶ በአስቸኳይ እንዲታረምና ዳግመኛ ግምት እንዲሰጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ በጽኑ ጠይቋል።

#ፖለቲካ መረጃ

Leave a Comment