banner

መንትያ እህትማማቾች በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

#FastMereja I ​በትምህርታቸው ትጉህና በሥነ-ምግባራቸው ለብዙዎች አርዓያ የነበሩት መንትያ እህትማማቾች ሰላማዊት ጥላሁን እና ሳምራዊት ጥላሁን በደረሰባቸው ከባድ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

​መነሻቸውን ከሀዋሳ ከተማ ያደረጉት መንትዮቹ ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ለመዝናናት ወደ ላንጋኖ መዝናኛ ማዕከል ሲያመሩ ነበር አደጋው የደረሰው። መዳረሻቸው ላይ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ በመኪናው ውስጥ የነበሩት ሁሉም ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል።

​ሰላማዊት ጥላሁን አደጋው እንደደረሰ ወዲያውኑ ሕይወቷ ያለፈ ሲሆን፤ ​ሳምራዊት ጥላሁን በበኩሏ ወደ ህክምና ማዕከል ተወስዳ እርዳታ ቢደረግላትም፣ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት ሕይወቷ ሊተርፍ አልቻለም።

​በሀዋሳ ነዋሪ የነበሩት እነዚህ እህትማማቾች፣ በአንድ ቀን ከጓደኞቻቸው ጋር ሕይወታቸው ማለፉ በቤተሰቦቻቸውና በሚያውቋቸው ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንን ፈጥሯል።

​ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን።

Leave a Comment