banner

የታሪክ ተረካቢዋ ህፃን እፁብድንቅ አንዱዓለም፤ የኬጂ ምረቃዋን ተከትሎ በዓድዋ መታሰቢያ አበባ አስቀመጠች

#FastMereja I ​የኬጂ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው ህፃን እፁብድንቅ አንዱዓለም፣ የትምህርት ምረቃዋን ታሪካዊ ካደረጉት ኩነቶች አንዱ የሆነውን የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ጉብኝት አድርጋለች። ታዳጊዋ በሙዚየሙ በመገኘት ለአድዋ ጀግኖች አክብሮቷን በመግለጽ አበባ አስቀምጣለች።

​የትምህርት ቤት ቆይታዋን በታላቅ ስኬት የቋጨችው እፁብድንቅ፣ የሀገሯን ታሪክ በወጉ ለመረዳትና ለጀግኖች አባቶች ያላትን ክብር ለማሳየት የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየምን መምረጧ ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ ድርጊቷ በህፃናት ዘንድ የሀገር ፍቅርን እና ታሪክን የመጠበቅን ባህል ለማነሳሳት እንደ አርዓያ የሚወሰድ ነው። ህፃን እፁብድንቅ በሙዚየሙ ጉብኝቷ ወቅት በጀግኖች ሙዚየም አበባዋን በማስቀመጥ፣ የነገዋ የሀገር ተረካቢ መሆኗን በይፋ አሳይታለች። የዚህ ዓይነቱ ተግባር ህፃናት ቀደምት አባቶቻቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት እንዲያስታውሱና የሀገር ባለውለታዎችን እንዲያከብሩ የሚያግዝ ነው።

#ማህበራዊ

Leave a Comment