banner

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለወጣቱ ባለሃብት ምህረተዓብ ሙሉጌታ እውቅና ሽልማት ሰጠ።

ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ለወጣቱ ባለሃብት ምህረተዓብ ሙሉጌታ እውቅና ሽልማት ሰጠ። ዛሬ ሐምሌ 08/2016 ዓ.ም በሜሪጆይ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ቢሮ በተከናወነ የእውቅና መረሃ ግብር ተከናውኗል።

የሜሪጆይ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ባደረጉት ንግግር “እስከዛሬ ካገኘዋቸው ሰዎች ምህረተዓብ የተለየ ነው እውነተኛ የእግዚዓብሔር አገልጋይ ነው፣ ሁሌም ከተቸገሩ ወገኖች ጎን ነው ሜሪጆይ ባስፈለገው ነገር ሁሉ ድጋፍ በማሰባሰብ እና ድጋፍ በማድረግ ግንባር ቀደም ነው፣ ይህ እውቅና ስለሚገባው ነው የሰጠነው” ብላለች።

አቶ ምህረተዓብ ሙሉጌታ ባደረገው ንግግር “ይህን እንድሰራ ያደረገኝ እግዚዓብሔር ነው ክብሩን ሁሉ እሱ ይውሰድ!” ብሏል።

ወጣቱ ባለሃብት አቶ ምህረተዓብ ሙሉጌታ በርካታ ድጋፎችን ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት በማድረግ ይታወቃል።

Leave a Comment