banner

በሀገሪቱ የሚገኘዉ ሆቴሎች ለዉጪ ሀገር ዜጎች የአገልግሎት ክፍያቸውን በዶላር ብቻ እንዲፈፅሙ ማድረግ ጀመሩ

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም የዉጪ ሀገር ፓስፖርት ያላቸው ዜጎች በሆቴሎች ለተጠቀሙበት አገልግሎቶች ክፍያ በዶላር እንዲፈፅሙ የሚያዝ ህግ ቢኖረዉም ለዓመታት ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱ ተሰምቷል። ሆቴሎች በዶላር ክፍያ እንዳይቀበሉ ተግዳሮት ሆኖባቸው ቆይቷል ከተባሉት ምክንያቶች መካከል በጥቁር ገበያዉ (Black Market) እና በመደበኛው የዉጪ ምንዛሪ መካከል ያለዉ ልዩነት እየሰፋ መሄዱ እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ የሚያደርገው ቁጥጥር ዝቅተኛ ሊሆን በመቻሉ ነዉ ተብሏል።

የአዲስ አበባ ሆቴሎች ማህበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት ” መመሪያው ከዚህ ቀደም በህግ ደረጃ የነበረ ቢሆንም ቁጥጥሩ ዝቅተኛ ነበር በዚህ ምክንያት የዉጪ ሀገር ዜግነት ያላቸዉ ቱሪስቶች ማረፊያቸውን በሚያደርጉበት ሆቴሎች ለተጠቀሙበት አገልግሎቶች ክፍያቸዉን በሂደት በብር ብቻ እንዲፈፅሙ” ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል ። አሁን ግን ብሔራዊ ባንክ በድጋሚ ቁጥጥሩን በማጠናከር በሰጠው አዲሱ ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ ክፍያቸውን በአሜሪካ ዶላር እንዲፈፅሙ እና ሆቴሎችም ይህንኑ መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸው ለማወቅ ተችሏል ሲል ካፒታል ዘገባ ተመልክተናል፡፡

Leave a Comment