banner

“ጎለ ሐርሜ” የተሰኘ ለእናቶች የተፃፈ አዲስ የአፋን ኦሮሞ መፅሐፍ ሊመረቅ ነው።

“ጎለ ሐርሜ” የተሰኘ በእናት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የአፋን ኦሮሞ መፅሐፍ ለገበያ ሊበቃ ነው። በደራርቱ ጫልቺሳ የተፃፈው ጎለ ሐርሜ መፅሐፍ በአማርኛ “የእናት ጓዳ” ማለት እንደሆነ ተነግሯል። ትኩረቱን በእናትነት ላይ አድርጎ የተፃፈ እንደሆነ ፃፊዋ ገልጻልናለች።

ከአፋን ኦሮሞ በተጨማሪ በቅርቡ በአማርኛ ተተርጉሞ ለገበያ እንደሚበቃ ተገልጿል። ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል።

መፅሐፉን ፅፎ ለማጠናቀቅ ሁለት አመት የፈጀ ሲሆን፣ ጎለ ሐርሜ 153 ገፅ ሲኖረው፣ በ300 ብር ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል። ከምርቃቱ በኋላ በመላው የኦሮሚያ አከባቢዎች ለሽያቅ ይቀርባል።

Leave a Comment