banner

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ተጀመረ

በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት ትብብር “አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ” በይፋ ተጀመረ፡፡

ኢኒሼቲቩን በሳይንስ ሙዚየም በመገኘት ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ዛሬ በይፋ የተጀመረው ንቅናቄ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በመሠረታዊ ዲጂታል ክህሎት ለማብቃት ያለመ ነው፡፡ በተለይም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ዳታ ሳይንስ፣ ዌብ ፕሮግራሚንግ እና አንድሮይድ ዴቬሎፕመንት ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡

ኢንሼቲቩ ቀጣዩ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው በማስቻል ለዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን መሆን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንቅናቄውን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ወጣቶች በመርሃ ግብሩ በመመዝገብ የዲጂታል ክሂሎት እንዲያገኙና በዘርፉ ዓለማቀፍ የማረጋገጫ ሰርተፊኬት ባለቤት አንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Leave a Comment