በቀድሞ ደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ሆቴል ቀበሌ ውስጥ ለፀጥታ ሥራ የተሰማሩ የፖሊስ አባላትን በመክበብ ተኩስ ከፍተው ሰባ አምስት የፖሊስ አባላትን በመግደል ወንጀል የተከሰሱ 75 ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ሲሆን 75 የፌደራልና የደቡብ ክልል ልዪ ኃይል የፖሊስ አባላትን በመግደል ወንጀል የተከሰሱ 30 ወንድና 1 ሴት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል ምድብ ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ቀርበው ነው የቅጣት ውሳኔው የተላለፈባቸው።
ችሎቱ የቅጣት ውሳኔውን ባስተላለፈበት ወቅት ተከሳሾቹ የመዋቅር ጥያቄአቸውን በኃይል ለማስመለስ በማሰብ ህገ-ወጥ መንገድ በታጠቁት የጦር መሳሪያ ለፀጥታ ስራ በተሰማሩ 75 የፖሊስ አባላት መግደላቸውን አስረድቷል።
በተጨማሪም 8 ማቁሰላቸው ፖሊስ በማስረጃ አስደግፎ ለሚመለከተው የህግ መላኩን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ መርማሪ ኮማንደር ዘሪሁን ክፍሌ ገልጸዋል።
በዚህም ጥይት በባጃጅ ሲያጓጉዝ ነበር የተባለ ተከሳሽን በስምንት አመት ጽኑ እስራት ሲቀጣው ሌሎቹ ሰለሳ ተከሳሾች የወንጀሉ ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆናቸውን በመረጋገጡ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል እንደተላለፈባቸዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።