😔😢
የተወለደው ከማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ካለው ሰፈር ፤ ያደገው ደግሞ በቤተክርስቲያኒቷ አፀደ ጊቢ ድጎማዋንና ስርዓቷን ተከትሎ ነው፤ ከኔ ጋር የተዋወቅነው የስድስት ዓመት ዕድሜችን ላይ ፩ኛ ክፍል አብረን ስንማር ነው።
ከ፩ኛ እስከ ፰ኛ ክፍል ቅዱስ ጊዮርጊስ ት/ቤት አንድ ክፍል ተምረናል። ፬ኛ ኤ ክፍል እያለ የሳይንስ ትምህርት መምህራችንንና የክፍል ሃላፊችን የነበሩት ቲቸር ገረመው ቀኖ አብረን አንድ ዴስክ ላይ እንድቀመጥ አደረጉን።
ጌች በ1981-1984 ባሉት ዓመታት በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ከመዘምራን አባላት አንዱም ነበረ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የ11ሰዓት ጉባኤ ቀድሞ የተጀመረው በወቅቱ ልደታ ቤ/ክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበሩት ብፅሁ አቡነ ገብርኤል ነበረ።
ያኔ ጌታቸውና ጓደኞቹ ከፍተኛ አስተባባሪ ነበሩ። ብፁዕነታቸው ጌታቸውን በመዝገብም በክርስትናም ስሙ እየጠሩ የሚያወድሱት የሚያበረታቱት ታዳጊ ነበረ።
ጌታቸው በኤለመንተሪ የጋራ የተማሪነት ዘመናችን ከአንድን ተማሪ ጋር ተጣልቶ አያውቅም። እሱ የሚታወቀው በቀልደኝነቱ (ኮሚዲያነቱ) ነበረ። እሱ ባለበት ሳቅ አለ። ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ላይ ደግሞ እጅግ ጎበዝ ያውም የደረጃ ተማሪ ሆኖ ሚኒስትሪን በከፍተኛ ነጥብ አልፏል።
ከዛ የሃይስኩል በኃላ አልተገናኘንም ነበረ። ስምንተኛ ክፍልን ካጠናቀቅን ከስምንት ዓመት በኃላ አብረን አንድ ክፍል የተማርን ሁሉ አሰባሰበን። ከልደታ እስከ ጦር ሃይሎች በእግሩ እየሄደ “ኑና እንገናኝ” የሚል ጥሪ ካርድ በተነ። ሁላችንም አንድ ክፍል የተማርን የጌችን ጥሪ አክብረን ያኔ ተገናኘን።
ያኔ ሰብስቦን ለምን በጓደኝነታችን ስም ጊቢ አንድ በጎ ስራ በጋራ እንሰራም? ብሎም ዝክረ ሀሳብ አቀረበ። አብዛኞቻችን የከፍተኛ ትምህርት ላይ የነበርንበት በመሆኑ ሰራተኞችም ባለመሆናችን ብስለቱም ባለመኖሩ ድንቁን ሀሳብ ትኩረት ሳንሠጠው ቀረን።
ጌች ከዚህ በፊት እንዳለው መፀሀፍ አንባቢነቱ ከልጅነቱ ይጀምራል ለኪነጥበብ የተጠራው ያኔ መሆኑን ያውቅም ነበረ። ጌታቸው ተማሪ እያለ 025 ሳንቲም መፅሀፍ እየተከራየ ያነብ ነበረ። ስምንተኛ ክፍል ላይ የእንግሊዘኛ ልብወለድ መፅሀፍትን ያነብ ነበረ። ኃላ ላይ እንደውም ያነበባቸውን ሁሉም መፅሀፍ ለሚኖርበት ለቀድሞ ከፍተኛ 4 ቀበሌ 49 ቤተ-መፅሀፍት አበርክቷል።
ጌታቸው የሰፈር ሰው ከታመመ ገንዘብ ከማሰባሰብ እስከ ማሳከም ብቻውን የሚሰራ እምነት የሚጣልበት ሰው ነበረ፤ የልደታ ልጆች ይህን በጎ ግብሩን ይመሰክሩለታል። ጌች በርካታ ፊልም ሰርቷል። ስራም ሰውም አይንቅም። ቀጠሮ አክባሪ ነው ።
ታድያ ምን እና እንዴት እንደ ሆነ ባላውቅም የአልኮል ሱሰኛ እንደሆነ አላውቅም፤ ለምን በዛ ደረጀ ለንግግሩና ለአዋዋሉ ሳይጨነቅ እንደቀረ፤ ለምን ህልሙ ጫፍ እንዳይደርስ የጎተተው ምን እንደሆነ ግራ እንደገባኝ ነው። አሁንም!
ጌች ያለበትን ከማን ጋር እንደሚኖርም ማወቅ አልቻልኩም፤ አድራሻውንም አላውቅም። ስልክ አለው ግን ሁሌ ዝግ ነው። የአሁኑ ጓደኞቹንም አላውቅም፤ እንደኔ ብዙ የድሮ ጓደኞቹ ፈልገነዋል።
ዛሬ ረፋዱ ላይ ግን ማረፉን ከአብሮ የክፍልና የትምህርት ቤት ጓደኛችን ከሆነው ተመስገን ካሳ ሰማሁ። (ተሜ ለጌታቸው የሰፈሩም ጓደኛው ነው)
የያኔ የትምህርት ቤት የልጅነት ጓደኛዬ ነፍስ በሰላም ትርፍ!😢
ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃ

10 comments
Rest in peace
Rip 😭
Rest in peace
Rest in peace
Rest in peace
Rest in peace
We can’t do anything rest in peace
Rest In Peace 😥😭
Rest in peace
Simany ant godanyaa ayidlakim
Rest in peace