0
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች ከ6 ቀበሌዎች በላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከ900 በላይ ቤቶች መዋጣቸውና ከ6ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።
የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሳሊ ሃሰን በአደጋው ምክንያት ከ1200 ሄክታር በላይ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት በዞኑ ከፍተኛ ስፍራዎች ከባድ ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የሚፈጠረው ጎርፍ ማረቆ ወረዳን አቋርጦ በኦሮሚያ ክልል በመቂ አልፎ ዝዋይ ሀይቅ ይቀላቀል የነበረ ቢሆንም ከዓመታት በፊት ለመስኖ በሚል በማረቆ ወረዳ የተሰራው የመስኖ ግድብ በከፍተኛ ደለል በመሞላቱ ምክንያት ውሃው መውራጃ ሲያጣ በአካበቢው የጎርፍ አደጋ እያስከተለ መሆኑ ተጠቁሟል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም በስልጤ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ 1650 ሰዎች መፈናቀላቸውን እንዲሁም በእንስሳት እና ሰብሎች ላይ ውድመት ማጋጠሙን መዘገባችን ይታወሳል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ነው የዘገበው።




2 comments
ወገኖቻችን አላህ ይድረስላቹ🤲😭
ሙስሊም ሳትሆኑ አትሙቱ