0
“ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ ሃና ማሪያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ ነበር ” የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 የሆቴል መስተንግዶ ሠራተኞች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ” ቀይ አፈር ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቀን 8፡20 ላይ ነው እንደደረሰ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
አንድ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ እግረኞችን ገጭቶ ባደረሰው አደጋ ነው የ3ቱ ሰራተኞች ህይወት ያለፈው።
ሟቾቹ ሶስቱም ሴቶች ሲሆኑ ዕድሜያቸው ከ25-30 ይገመታል።
ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ ” ሃና ማሪያም ” ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ ነበር።
ከሟቾቹ ጋር አብራ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ሴት እራሷን ስታ ሕክምና እየተከታተለች ትገኛለች።
በበዓል ወቅት መሰል አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እና በእርጋታ እንዲያሽከረክሩ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።
ኤፍቢሲ


8 comments
RIP
Betam yikebdal
Rip 😔, lendezi aynet adegawoch Gera mesmer yezo meguaz betam bezu edil yesetal, gen yeketemaw sew bezu tekuret aysetewm
በጣም ያሳዝናል 😭😭😭😭
ነፍስ ይማር ።
ነብስ ይማር
የከባድመኪና ሹፌሮች ግን ተረጋግተው ቢነዱ የስንቱን ቤት ጥቁር አለበሱት 😭😭😭
RIP baxam yamal