banner

በሐረር ከተማ ትውልድን ከአደንዛዥ ዕፅ ሱስ እንታደግ የሚል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

#FastMereja
ላግዛት የበጎ አድራጎት ድርጅት በሐረሪ ክልል ትውልድን ከአደንዛዥ ዕፅ ሱስ እንታደግ የሚል ፕሮጀክት ዛሬ መስከረም 10/2017 ዓ.ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ሆነ።

የፕሮጀክቱ ግቦች በክልሉ በሚገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ከትምህርት ቤቶች ውጪ የሚገኘውን የህብረተሰብ አካል ስለ አደንዛዥ ዕፅ ሱስ አስከፊነት ግንዛቤ መፍጠር፣ በክልሉ የሚገኙ በሱስ የተጠቁ ዜጎች የሚታከሙበት ክሊኒክ እና ከሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ማቋቋም፤ እንዲሁም ወጣቶች ለአደንዛዥ ዕዕ ሱስ እንዳይጋለጡ የተለያዩ የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠናዎችን መስጠት እና የስራ ዕድሎችን ማመቻቸት እንደሆነ የማሀበሩ አመራሮች ተናግሯል።

የክልሉ ጤና ቢሮ፤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ የክልሉ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክልሉ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት ከአደንዛዥ ዕዕ ሱስ የጸዳ እና አምራች የሆነ ብቁ ዜጋ መፍጠርን ዋና ራዕይ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልጿል።

ለዚህም ስራ የሐረሪ ሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነው የኢህሳን አብዱሰላም ልጅ የሆነው ዊሳም ኢህሳንን የክብር አምባሳደር በማድረግ ስራ አስጀምሯል።

ላግዛት የበጎ አድራጎት ድርጅት በ2014 ዓ.ም. የተቋቋመ ሀገር በቀል ቦርድ-መር የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ የስሙ ትርጉም በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን እምቅ ሀይል በመጠቀም ጤነኛ እና ብቁ ትውልድን በማፍራት የሀገራችን የኢትዮጵያን የወደፊት እድገት ማገዝ ማለት ነው፡፡





2 comments

Yonas Tesfaye September 20, 2024 - 3:19 pm

አመራሩ የእውነት ከልቡ ሚሰራ ከሆነ መጀመሪያ ወጣቱን በማደራጀት ሰፋፊ የስራ እድሎችን መፈጠር አለበት አለበለዚያ ስራ ባሌለበት ወጣቱ ዬት ይሂድ

Reply
Ashebir Demie September 20, 2024 - 4:04 pm

እስከማውቀው ድረስ ለእንደዚህ አይነት ተለእኮ አምባሳደር የሚሆኑ ሰዎች በመልካም ስም:ዝናና ታዋቂነት ተጽእኖ ሊያሳድሩና አመለካከት ሊቀርጹ/opinion form ማድረግ የሚችሉ ሠዎች እንጂ “የእከሌ ልጅ” በማለት አይደረግም። Ot look you are not serious from the beginning

Reply

Leave a Comment